በሁለተኛው የስልጣን ዘመናቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ትልቅ ዲፕሎማሲያዊ ጉዞ ለማድረግ ሳዑዲ አረቢያ የገቡት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ሳዑዲ አረቢያ፣ ኳታር እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በሚያደርጓቸው የአራት ቀናት ጉዞዎች በአሜሪካ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ አዲስ ኢንቨስትመንት እንደሚያስገኝ ተስፋ አድርገዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ የፕሬዚዳንቶች ስልጣን ከያዙ በሗላ ወደ እንግሊዝ፣ ካናዳ ወይም ሜክሲኮ ለጉብኝት የሚሄዱበትን መርህ በመጣስ ትራፕ፣ የመጀመሪያ ትልቅ የሚባለው ጉብኝት ወደ ሳዑዲ አረቢያን አድርገዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
