በመላው ዓለም ለሚገኙ የድሬዳዋ ተወላጆች እና ወዳጆች የተላለፈ የበጎ አድራጎት የእራት ጥሪ
ላለፉት ስምንት ዓመታት፣ በድሬዳዋ ከተማ ለሚገኙ ዐቅመ ደካሞች እና ችግረኛ ተማሪዎች እገዛ ሲያደርግ የቆየው “የድሬዳዋ ልጆች እና ወዳጆች ዓለም አቀፍ ማኅበር” ፣ ዘንድሮም ድጋፍ የሚያሰባስብበትን የራት ምሽት ኦገስት 30 ቀን 2025 ዓ.ም. አዘጋጅቷል፡፡
በመላው ዩናይትድ ስቴትስ እና በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን፣ የመተሳሰብ እና የአንድነት ተምሳሌት በኾነችው የድሬዳዋ ከተማ የሚኖሩ ችግረኞችን ለመደገፍ በሚከናወነው በዚኹ ዓመታዊ የበጎ አድራጎት የራት ምሽት ላይ በመሳተፍ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ ዓለም አቀፍ ማኅበሩ የግብዣ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
ከጊዜው ማጠር የተነሳ በተለይም፣ በዋሽንግተን ዲሲ፣ ሜሪላንድ እና በቨርጂኒያ አካባቢ የምትገኙ የድሬዳዋ ተወላጆች እና ወዳጆች፣ በማዕድ ዙሪያ በመገናኘት ያለንን ለችግረኛ ወገኖቻችን ለማካፈል ጥብቅ ቀጠሮ በያዝንበት የራት ምሽት ላይ አንዳችኹም እንዳትቀሩ ዓለም አቀፍ ማኅበሩ በአክብሮት ይጋብዛል፡፡ የመዝናኛ ዝግጅቶችም በምሽቱ ይቀርባሉ።
$100 የሚያስከፍለውን የመግቢያ ትኬት በኦንላይን አስቀድሞ መግዛት ይቻላል። http://bit.ly/47Ib12s
የመርሐ ግብሩ ቀንና ሰዓት፡-
ኦገስት 30 ቀን 2025 ዓ.ም.
አድራሻ፡- 3149 Glen Carlyn RD
Falls Church, VA 22041
ለበለጠ መረጃ- (703) 981-3876 ወይም (571) 814-1103 ላይ መደወል ትችላላችኹ!
“የድሬዳዋ ልጆች እና ወዳጆች ዓለም አቀፍ ማኅበር”
