የጃፓን መንግስት ለኢትዮጵያ ከ63ሺህ ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ድጋፍ አደረገ

Date:

የጃፓን መንግስት ለኢትዮጵያ አርሶ አደሮች ተደራሽ የሚሆን ከ63ሺህ ኩንታል በላይ የዩሪያ አፈር ማዳበሪያ ድጋፍ አድርጓል።

የማዳበሪያ ርክክቡ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ሶፊያ ካሳ፣ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው እና በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ሺቢታ ሂሮናሪ በተገኙበት ተከናውኗል።

የግብርና ሚኒስትር ዴኤታዋ ሶፊያ ካሳ የጃፓን መንግስት ላደረገው ድጋፍ አመስግነው፤ የአፈር ማዳበሪያው ለታለመለት ዓላማ እንዲውል ሚኒስቴሩ ይሰራል ብለዋል።

በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ሺቢታ ሂሮናሪ በበኩላቸው፤ መንግስታቸው ግብርናን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ስለመናገራቸው የኢ.ቢ.ሲ መረጃ ያመለክታል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት በዛሬ ዕትሟ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ነሔሴ 16 2018 ዓ.ም ገበያ...

ቱርክ ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ አወጣች

ቱርክ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ ዓለም አቀፍ...

በመቀለ የሚካሄደው የአሸንዳ በዓል የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተሰረዘ

በትግራይ በርካታ ታዳሚ በሚገኝበት በየዓመቱ የሚከበረው የአሸንዳ ባህላዊ በዓል...

የኢትዮጵያ ፖስታ 3 ሺሕ የሚጠጉ ቅርንጫፎቹን ወደ ባንክ ኤጀንትነት ለመቀየር እንቅስቃሴ ጀመረ

የኢትዮጵያ ፖስታ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ 3 ሺሕ በሚጠጉ ቅርንጫፎቹ...