የገቢዎች ቢሮ የሂሳብ ባለሙያዎች የሙያ ፈቃድ እንዲሰረዝ ጠየቀ

Date:

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የመንግስትን ጥቅም በሚጎዳ መልኩ ከፍተኛ የገንዘብ ግድፈት ፈጽመዋል ያላቸው የ10 የሂሳብ ባለሙያዎችና ኦዲተሮች የሙያ ፈቃድ እንዲሰረዝ ለኢትዮጵያ የሂሳብና ኦዲት ቦርድ ጥያቄ አቀረበ።

የቢሮው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ እነዚህ ባለሙያዎች በ2017 በጀት ዓመት የ13 ግብር ከፋዮችን መዝገብ በማዘጋጀት ላይ እያሉ በቅድመ ኦዲት ወቅት የግብር ስወራ ሊያስከትል የሚችል ከፍተኛ ስህተት ተገኝቶባቸዋል።

ይህ እርምጃ የተወሰደው በታክስ አስተዳደር አዋጅ 983/2008 መሰረት ነዉ ተብሏል።

ከዚህ በተጨማሪ፣ ቢሮው የሂሳብ መዝገብ አዘገጃጀት ላይ የሚታዩ ስህተቶችን ለመከላከል ከቦርዱና ከሙያ ማኅበራት ጋር በመተባበር መመሪያዎችን አዘጋጅቶ ማሰራጨቱን ገልጿል።

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ፈቃዳቸው እንዲሰረዝ በተጠየቁት ባለሙያዎች የተዘጋጁ የሂሳብ መዝገቦችን እንደማይቀበል ያሳወቀ ሲሆን ግብር ከፋዮችም የሙያ ስነ-ምግባርን በሚጠብቁ ባለሙያዎች የተዘጋጀ መዝገብ እንዲያቀርቡ አሳስቧል።

CapitalNews

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...