በሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ለዓመታት በአድማጮች ልብ የተቀመጠው ተወዳጁ ጋዜጠኛ እሸቴ አሰፋ “መቆያ” የራዲዮ ዝግጅት አሁን “እነሆ መቆያ” በሚል ርዕስ በመፅሀፍ መልክ ለአንባቢያን ቀርቧል።
“መቆያ” ስሜት የሚነኩ ታሪኮችን፣ የሕይወት ትምህርቶችን እና የሰው ልጅ ተሞክሮዎችንሬጠሬ በልዩ የአቀራረብ መንገድ ሲያቀርብ የቆየ ታላቅ የራዲዮ ድምፅ ነበር።
አሁን ግን ያ የልብ ድምፅ በጽሁፍ ተሰብስቦ በመፅሀፍ መልክ ተዘጋጅቷል፤ ከድምፅ ዓለም ወደ ጽሁፍ ዓለም የሚያስገባ ልዩ የስሜት ጉዞ ይሰጣል።የ“መቆያ” መፅሀፍ በጃፋር የመፅሀፍ መደብር ይገኛል።
