“የፖለቲካ ተሳትፎ መመሪያ መፅሐፍ” ተመረቀ

Date:

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት (KRF Norway) ከተሰኘው አጋር ድርጅት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው “የፖለቲካ ተሳትፎ መመሪያ መፅሐፍ” ተመረቀ ።

የመመሪያው መፅሐፍ የኢትዮጵያ ፖለቲካን ለማሳደግ ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረክታል ተብሎለታል።

በምረቃ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ነዋይ መፅሐፉ ከምርጫ ሂደቱ ጋር ተያይዞ ልዩ ግብአት፣ ተሞክሮ እና አሰራሮችን የያዘ በመሆኑ ለፖለቲካ ፓርቲዎች ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ሰሎሞን አየለ መፅሐፉን በርካታ ፋይዳዎች እንዳሉት ተናግረዋል።

የምረቃ ፕሮግራሙ አካል የሆነ የፓናል ውይይት በጉዳዩ ዙሪያም ተካሂዷል። ተሳታፊዎች ይህ መመሪያ መፅሐፍ ከዚህ ቀደም በተደራጀ መልኩ ያልነበረ በመሆኑ በኢትዮጵያ ውስጥ አካታች፣ ሰላማዊ እና የሰለጠነ የፖለቲካ ተሳትፎን ለማበረታታት ትልቅ ግብአት እንደሚሆን ነግረውናል።

መፅሐፉ በሰባት ክፍሎች የተዋቀረ ሲሆን የፖርቲዎች አመራር፣ የፖሊስ ቀረጻ ኮሙኒኬሽን የሚዲያ አጠቃቀም አካታችነት የጋራ ምክር ቤቶች ተሳትፎን አካቷል።

(አራዳ ኤፍ ኤም)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...