የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና መሰጠት ጀመረ

Date:

የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት በሁሉም የመፈተኛ ማዕከላት መሰጠት መጀመሩን፤ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል፡፡

ማጠናቀቂያ ፈተናው በኦንላይን እና በወረቅት በመሰጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ የመጀመሪያ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተና በዛሬው ዕለት በሁሉም የመፈተኛ ጣቢያዎች መሰጠት ጀምሯል።

በዚህም መሠረት ዘንድሮው በተፈጥሮ ሳይንስና በማህበራዊ ሳይንስ በአጠቃላይ 608 ሺሕ 588 ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ የተገለጸ ሲሆን፤ 140 ሺሕ የሚጠጉ ተማሪዎች ፈተናውን በኦንላይን እንሚወሰዱ ተመላክቷል፡፡

የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የማጠናቀቂያ ፈተና በአራት ዙሮች የሚሰጥ ሲሆን፤ ከሰኔ 23 ጀምሮ እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል፡፡

በዚህ መሠረት የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከሰኔ 23 እስከ 30 ድረስ እንዲሁም፤ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ደግሞ ከሐምሌ 1 እስከ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ፈተናውን እንደሚወስዱ ተገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...