የ2018 በጀት ዓመት 350.13 ቢሊዮን ብር ሆኖ ጸደቀ !!

Date:

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 በጀት ዓመት 350.13 ቢሊዮን ብር ሆኖ በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በሙሉ ድምፅ ፀደቀ።

ይህ በጀት ካለፈው የበጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ108 ቢሊዮን ብር ወይም የ45 በመቶ ዕድገት ያሳየ መሆኑን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ አብዱል ቃድር ሬድዋን አስታውቀዋል።

አቶ አብዱል ቃድር ሬድዋን የበጀት ረቂቅ አዋጁን ለምክር ቤቱ ባቀረቡበት ወቅት፣ በጀቱ የሚሸፈንባቸውን ዋና ዋና የፋይናንስ ምንጮች ዘርዝረዋል።

በዚህም መሰረት፡-

  • ከታክስ ከ238 ቢሊዮን ብር በላይ ወይም 68 በመቶ
  • ከማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ ከ56 ቢሊዮን ብር በላይ
  • ታክስ ካልሆነ ገቢ ከ46 ቢሊዮን ብር በላይ
  • ከመንገድ ፈንድ 1.8 ቢሊዮን ብር
  • ከውጭ ብድርና እርዳታ ደግሞ 6.98 ቢሊዮን ብር እንደሚገኝ ተገልጿል።

ከፀደቀው አጠቃላይ በጀት ውስጥ፣ 70.35 በመቶ ለካፒታል በጀት፣ 26.22 በመቶ ለመደበኛ በጀት እንዲሁም 3.43 በመቶ ለመጠባበቂያነት መያዙ ታውቋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአርቲስት ጥላሁን ገሠሠ መታሰቢያ ሐውልት ተመረቀ

ለኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ዕድገት ወደር የሌለው አስተዋጽኦ ላበረከተውና የሙዚቃው...

ሕወሓት ድብረጺዮንን የክልሉ ፕሬዚዳንት አድርጎ መረጠ

የክልሉ ፕሬዚዳንት ተደርገው የተመረጡት  ድብርጺዮን ገ/ ሚካዔል (ዶ/ር)  ቃለ...

” ኢራን ከምድረ ገጽ ትጠፋለች ” – ትራምፕ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፎክስ ኒውስ ቴሌቪዥን ጋር ቃለ...

የአርበኞች ድል መታሰቢያ እና የዛሬው ትውልድ ለሕብረት ያለው አቋም

የጥንት ኢትዮጵያዊያንአርበኞች ድል 85 ኛው ዓመት መታሰቢያ ሚያዚያ...