• ሙሉ የኔትፊልክስ ፊልሞችን በአንድ ሰከንድ ለማውረድ ያስችላል
ቢዝነስ ቱዴይ እንደዘገበው፤ የጃፓን ተመራማሪዎች በሰከንድ 1 ነጥብ 02 ፔታቢትስ የኢንተርኔት ፍጥነት በማስመዝገብ የዓለም ሪከርድ መስበር ችለዋል፡፡
ግኝቱ የ6ጂ ኔትወርኮችንና የባህር ውስጥ ገመዶችን የኢንተርኔት ፍጥነት በማሻሻል ሙሉ የኔትፊልክስ ፊልሞችን በአንድ ሰከንድ ውስጥ ለማውረድ እንደሚያስችል ዘገባው አመልክቷል።
አሁን ያለውን የፋይበር ኦፕቲክ ቴክኖሎጂን የሚጠቀመው አዲሱ ግኝት፤ በዓለም ዙሪያ ሰዎች መረጃ የሚጋሩበትን መንገድ፣ የኮምፒውተርና የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አጠቃቀምን በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሻሽል ተነግሯል፡፡
