የ8ኛው “ንባብ ለሕይወት!” ዓመታዊ የመጻሕፍት አውደ ርዕይ ጋዜጣዊ መግለጫ

Date:

ሐምሌ 20/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት እና ንባብ ለህይወት ኢትዮጵያ ፕሮጀክት በጋር የንባብ ሳምንት እና ዓመታዊ የመጻሕፍት አውደ ርዕይ ከሐምሌ 23 እስከ ሐምሌ 26/2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ሊያካሒዱ እንደሆነ አዘጋጆቹ ገልጸዋል፡፡

ጋዜጣዊ መግለጫውን በማስመልከት ንግግር ያደረጉት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሠርፀ ፍሬስብሐት የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት በመላው ኢትዮጵያ የንባብ ባህል እንዲጎለብትና ማህበረሰቡ ከዕውቀት ጋር እንዲገናኝ ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረገ የሚገኝ ተቋም መሆኑን ተናግረዋል።

ተቋሙ ይህንን አገራዊ ዓላማ ይበልጥ ለማሳካት በዘንድሮው ኤግዚቢሽን ላይ በስፋትና በልዩ ትኩረት በመሳተፍ አገልግሎቶቹን ለአንባቢያን ያስተዋውቃል ብለዋል።

“ንባብ ለሕይወት!” የመጻሕፍት አውደ ርዕይ ዘንድሮ ለ8ተኛ ጊዜ የተሰናዳና አውደ ርዕዩ ከሐሙስ ሐምሌ 23 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ እሁድ ሐምሌ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ለአራት ተከታታይ ቀናት በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በደመቀ ሁኔታ ይካሔዳል።

በዘንድሮው የ“ንባብ ለሕይወት” አውደ ርዕይ ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ ደራሲያን፣ የመጻሕፍት አታሚዎች፣ አሳታሚዎችና አከፋፋዮች በስፋት እንደሚሳተፉ እና ለዝግጅቱ ልዩ ትኩረት በመስጠት የሚሳተፉ ስመጥር ተቋማት እንዳሉም አመላክተዋል፡፡

በአውደ ርዕዩ ላይ አንጋፋና ወጣት ደራሲያን በየዕለቱ ከአንባቢያን ጋር የሚገናኙበት የፊርማ እና የፎቶ ፕሮግራም ይኖራል፡፡

የተመረጡ የውይይት ርዕሶች ንባብ በዘመነ ሰውሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence)፤ንባብና ቱሪዝም፤የሙሉ ጊዜ ፀሀፊነትና እናትነት፤ የሙሉ ጊዜ ፀሀፊነትና እናትነት፤ ንባብ በማረሚያ ቤቶች እና ንባብና ክረምት በሚሉ ርዕሰ ጉዳዩች ውይይት የሚደረግበት ሲሆን በተጨማሪም በታዋቂው ደራሲ አዳም ረታ የሥነ-ጽሑፍ አበርክቶና ሁለንተናዊ ሥራዎች ላይ የሚያተኩር ልዩ ጥናታዊ ጽሑፍ ለታዳሚው የሚቀርብበት እንደሆነም ጠቁሟል።

ዝግጅቱ ህጻናትንም ያካተተ እንደሆነ ከሐምሌ 24 እስከ 26/2018 ዓ.ም በተለይ በጠዋቱ ክፍለ ጊዜ በልጆች ሥነ-ጽሑፍ እና ንባብ ላይ የሚያተኩሩ ማራኪ መርሐ ግብሮች መዘጋጀታቸውንና መግቢያው በነጻ እንደሆነና መጻሕፍትን በቅናሽ ዋጋ መግዛት የሚያስችሉ የመጻሕፍት የቅናሽ ኩፖኖች መዘጋጀታቸውም ጠቁመዋል።

በመጨረሻም አዘጋጆቹ ለመላው የመጻሕፍት ወዳጆች፣ ተማሪዎች፣ ወላጆችና የሥነ-ጽሑፍ አፍቃሪያን በቀኑ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በመገኘት የዚህ ታላቅ ዝግጅት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪያቸውን አስተላልፈው ጋዜጣዊ መግለጫው ተጠናቋል።

ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችንን ይከታተሉ!!
ቴሌግራም: https://t.me/wamezeker
ድረገጽ: https://www.nala.gov.et/
ዩቲዩብ: https://www.youtube.com/@nationalarchivesandlibrary7572
ፌስቡክ: https://web.facebook.com/Wemezekr
ትዊተር:https//@wemezekr
ቲክቶክ፡https፡/tiktok.com/@wemezekrnals
ኢ-ሜይል፡- https://www.nala

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ዘመን ባንክ ከ10 ቢሊየን ብር በላይ ያልተጣራ ትርፍ አገኝ

ዘመን ባንክ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ10.2 ቢሊየን ብር በላይ...

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የ25 ዓመታት ሀገር አቀፍ ማስተር ፕላን ጥናት ይፋ አደረገ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኃይል አቅርቦት ሥርዓት ወደ ዘመናዊና ዲጂታል...

ኢራን ላይ የተደረገው ጦርነት አሜሪካን እንዳዳከማት ባለስልጣኑ ተናገሩ

የአሜሪካው ኮንግረስ አባል ቶማስ ማሲ፣ የትራምፕ አስተዳደር በኢራን ላይ...

የቲክቶኮ ድምቀት በመድረክ ትያትር መጣ!

ቴዎድሮስ ሸዋንግዛው በኢትዮጵያ የድራማ ታሪክ ውስጥ በአዲስ አይነት መንገድ...