የአፍሪካ ቁጥር አንድ ባለጸጋ አሊኮ ዳንጎቴ፣ ንብረት የሆነው የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ፣ በዓለም ዙሪያ የነዳጅ ሽያጩን በማፋጠን አስደማሚ ስኬት እየተቀዳጀ መሆኑ ተነገረ፡፡
ዳንጎቴ ፔትሮሊየም ሪፋይነሪ፤ በሳውዲ አራምኮ እና በኩዌት ነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካዎች ላይ በተፈጠረው የጥገና ችግር ምክንያት የተከሰተውን የነዳጅ እጥረት ለመሙላት የነዳጅ ምርቶችን በስፋት ወደ ውጭ መላክ ጀምሯል።
በነሐሴ ወር ላይ ብቻ፣ በሌጎስ የሚገኘው የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ፣ ከፍተኛ መጠን ያለው ቤንዚን፣ ናፍጣና የአውሮፕላን ነዳጅ ወደ መካከለኛው ምስራቅና ሌሎች ሀገራት መላኩ ተዘግቧል።
በኢንዱስትሪው ውስጥ ያሉ አንዳንድወገኖች በፋብሪካው አፈፃፀም ላይ ጥያቄ ቢያነሱም፣ የዳንጎቴ ግሩፕ በመጪው ዓመት ታህሳስ ወር ላይ በቀን 700,000 በርሜል ለማምረት እየሰራ መሆኑን ገልጿል።
ፋብሪካው በአሁኑ ጊዜ ወደ አውሮፓ፣ አሜሪካና ምዕራብ አፍሪካ የነዳጅ ምርት እየላከ ሲሆን፤ በ2026 የ30 ቢሊዮን ዶላር ገቢ እንደሚያስገኝ ይጠበቃል፡፡
