ድምጽ ሳያሰሙ የእንባ ዘለላዎችን አፍስሰዋል

Date:

በሽኝት ሂደት ከታዩ አንጀት የሚበሉ ትእይንቶች መካከል አንዱ የኦርቶዶክስ አባት የአባ ማቲያስ መንሰፍሰፍና ለቅሶ ነበር። ድምጽ ሳያሰሙ የእንባ ዘለላዎችን አፍስሰዋል።

አባ ማቲያስ ከሙፍቲ ጋር በቅርበት የሰሩ ስለሆኑ በዚያ ታላቅ ሰው ስብዕና ውስጥ የታመቀውን እዝነት፣ሰብአዊነት፣ጥበብ፣ለዛና የሀገር ፍቅር ጠንቅቀው ያውቃሉ።

አሁን ያ ተስረቅራቂ የዕውነት ድምጽ፣ ያ ባለለዛ አንደበት፣ ያ ገደብ አልባ ፍቅር፣ያ አስታራቂ ስብዕና ወደማይቀርበት ዓለም ተሸጋግሯል። እዝነት ታላቁን ልጇን አጥታለች። ሀገር አሳቢ አባቷን ተነፍጋለች።

ይህ እንደአባ ማቲወስ ባለ ስብዕና ውስጥ የሚፈጥረው የሀዘንና አጋር የማጣት ስሜት ጥልቅና ብርቱ እንደሚሆን ዕሙን ነው። “ክንዴ ክንዴ” እያሉ አልቅሰው እንዳይወጣላቸው ያሉበት ዕድሜና የሀላፊነት ደረጃ አይፈቅድላቸውም።

እናም የእንባ ዘለላዎች የውስጣቸው ህመምና ቃጠሉ መልዕክተኛ ሆነው እርሳቸውን ሳያስፈቅዱ በጉንጮቻቸው ላይ ፈሰሱ። ሰውነታቸው የአባትነት ክብራቸውን አሸንፎ እንደሰው አለቀሰ። ሰውነት እንደዚህ ነው። “ሰው እንሁን፤ሰውነት ይቀድማል!!!”

አምባሳደር ኡስታዝ ሀሰን

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በመንገድ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ

አደጋው የደረሰው ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ...

ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች  565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት...

የአማርኛ ቋንቋ እውነተኛ ምንጭ ቤተ መንግሥት ሳይሆን ሕዝብና ሠራዊት ነው

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም አዘጋጅነት ከስድስት...