የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን 2ለ0 ተሸንፏል

Date:

የኢትዮጲያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ሁለተኛ ዙር የመጀመሪያ ጨዋታዉን በታንዛኒያ አዛም ኮምፕሌክስ ስታዲየም ከታንዛኒያ ጋር  አድርጎ ሁለት ለምንም ተሸንፏል።

ሉሲዎቹ በጨዋታዉ ሙሉ ብልጫ የተወሰደባቸዉ ሲሆን በእንቅስቃሴ እረገድ እንዲሁም ደግሞ በመከላከሉ በኩል በእጅጉ ተዳክመዉ ታይተዋል።

የኢትዮጲያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የመልሱን ጨዋታ በድሬደዋ ስታዲየም በቀጣይ ሳምንት ማክሰኞ የሚከዉን ሲሆን ከ14 አመት በኋላ ዳግም ወደ አፍሪካ መድረክ ለመመለስ ከ 3 በላይ ግቦችን አስቆጥሮ ማሸነፍ ይጠበቅበታል።

ሉሲዎቹ በመጀመሪያዉ ዙር ከሜዳቸዉ ዉጭ በዩጋንዳ 2ለ0 ተሸንፈዉ በመልሱ ጨዋታ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይህንን ዉጤት በመቀልበስ ወደ ዚህኛዉ ዙር እንዳለፉ የሚታወስ ሲሆን በሳምንቱስ ጨዋታ ይህንን ደግመዉ ዳግም ታሪክ ይፅፉ ይሆን ወይ የሚለዉ ተጠባቂ ነዉ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በመንገድ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ

አደጋው የደረሰው ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ...

ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች  565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት...

የአማርኛ ቋንቋ እውነተኛ ምንጭ ቤተ መንግሥት ሳይሆን ሕዝብና ሠራዊት ነው

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም አዘጋጅነት ከስድስት...