ዶ/ር ተሻለ አሰፋ “ቲያትር ቤቶች መጠጥ ቤት እንዳይሆኑ ያስፈራኛል”

Date:

ታዋቂው የቴአትር ጥበባት መምህርና አዘጋጅ ዶ/ር ተሻለ አሰፋ “ሆቴሎችም ቲያትር ማሳያ ሆነው ቲያትር ቤቶች መጠጥ ቤት እንዳይሆኑ ያስፈራኛል” ሲል ትዝብቱን ተናግሯል።

የዶ/ር ተሻለ አሰፋ ሙሉ ሀሳቡ እንደሚከተለው ይቀርባል” ባለፈው ሐሙስ “የእራት ግብዣው” የተሰኘውን ቲያትር በዓለም ሲኒማ እየተመለከትኩ ሀሳቤ ለሁለት ተከፍሎ ነበር።

በአንድ ወገን በቲያትሩ ስደሰት በሌላ በኩል ደግሞ እስካሁን ድረስ አልላቀቅ ካለኝ ጥያቄ ጋር ስሟገት ነበር። ዓለም ሲኒማ ቲያትር ቤት አይደለምኮ።

ታዲያ ለምንድነው በርካታ ድንቅ ስራዎችና በሳል ባለሙያዎች ወደዚያ የሄዱት? (የተሰደዱት ብዬ ነገሩን ማጮህ አልፈለግኩም)። ይሄ ጥያቄ ከዚህ በፊት በሌሎች ባለሙያዎችም ሲጠየቅ ሰምቻለሁ። መልስ እጠብቅ ነበር።

በተለይ ዋና ስራችሁ ቲያትር መስራት ከሆነ ቲያትር ቤቶች። መጠበቅ ብቻ ሳይሆን ደጃችሁ ድረስ መጥቼ ተሟግቻለሁ። መልስ  አላገኘሁም። እንዳይረፍድ እሰጋለሁ። በዚህ የሚቀጥል ከሆነ ሲኒማዎች ብቻ ሳይሆኑ ሆቴሎችም ቲያትር ማሳያ ሆነው ቲያትር ቤቶች መጠጥ ቤት እንዳይሆኑ ያስፈራኛል። ሙያው ታላቅ ነው። ክብር ስጡት፤ ወይም ክብር ሰጥተውት ዋጋ እየከፈሉለት ያሉትን ባለሙያዎች አክብሯቸው። ይብቃኝ መሰለኝ። ለማንኛውም የ”የእራት ግብዣው” ቲያትር ተሳታፊዎች በሙሉ ድንቅ ስራ ሰርታችኋልና እንኳን ደስ አላችሁ።

ዶ/ር ተሻለ አሰፋ “ቲያትር ቤቶች መጠጥ ቤት እንዳይሆኑ ያስፈራኛል” ሲል ተናገረ

ታዋቂው የቴአትር ጥበባት መምህርና አዘጋጅ ዶ/ር ተሻለ አሰፋ “ሆቴሎችም ቲያትር ማሳያ ሆነው ቲያትር ቤቶች መጠጥ ቤት እንዳይሆኑ ያስፈራኛል” ሲል ትዝብቱን ተናግሯል።

የዶ/ር ተሻለ አሰፋ ሙሉ ሀሳቡ እንደሚከተለው ይቀርባል” ባለፈው ሐሙስ “የእራት ግብዣው” የተሰኘውን ቲያትር በዓለም ሲኒማ እየተመለከትኩ ሀሳቤ ለሁለት ተከፍሎ ነበር።

በአንድ ወገን በቲያትሩ ስደሰት በሌላ በኩል ደግሞ እስካሁን ድረስ አልላቀቅ ካለኝ ጥያቄ ጋር ስሟገት ነበር። ዓለም ሲኒማ ቲያትር ቤት አይደለምኮ።

ታዲያ ለምንድነው በርካታ ድንቅ ስራዎችና በሳል ባለሙያዎች ወደዚያ የሄዱት? (የተሰደዱት ብዬ ነገሩን ማጮህ አልፈለግኩም)። ይሄ ጥያቄ ከዚህ በፊት በሌሎች ባለሙያዎችም ሲጠየቅ ሰምቻለሁ። መልስ እጠብቅ ነበር።

በተለይ ዋና ስራችሁ ቲያትር መስራት ከሆነ ቲያትር ቤቶች። መጠበቅ ብቻ ሳይሆን ደጃችሁ ድረስ መጥቼ ተሟግቻለሁ። መልስ  አላገኘሁም። እንዳይረፍድ እሰጋለሁ። በዚህ የሚቀጥል ከሆነ ሲኒማዎች ብቻ ሳይሆኑ ሆቴሎችም ቲያትር ማሳያ ሆነው ቲያትር ቤቶች መጠጥ ቤት እንዳይሆኑ ያስፈራኛል።

ሙያው ታላቅ ነው። ክብር ስጡት፤ ወይም ክብር ሰጥተውት ዋጋ እየከፈሉለት ያሉትን ባለሙያዎች አክብሯቸው። ይብቃኝ መሰለኝ። ለማንኛውም የ”የእራት ግብዣው” ቲያትር ተሳታፊዎች በሙሉ ድንቅ ስራ ሰርታችኋልና እንኳን ደስ አላችሁ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአርቲስት ጥላሁን ገሠሠ መታሰቢያ ሐውልት ተመረቀ

ለኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ዕድገት ወደር የሌለው አስተዋጽኦ ላበረከተውና የሙዚቃው...

ሕወሓት ድብረጺዮንን የክልሉ ፕሬዚዳንት አድርጎ መረጠ

የክልሉ ፕሬዚዳንት ተደርገው የተመረጡት  ድብርጺዮን ገ/ ሚካዔል (ዶ/ር)  ቃለ...

” ኢራን ከምድረ ገጽ ትጠፋለች ” – ትራምፕ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፎክስ ኒውስ ቴሌቪዥን ጋር ቃለ...

የአርበኞች ድል መታሰቢያ እና የዛሬው ትውልድ ለሕብረት ያለው አቋም

የጥንት ኢትዮጵያዊያንአርበኞች ድል 85 ኛው ዓመት መታሰቢያ ሚያዚያ...