የገቢዎች ሚኒስቴር የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ በቢሾፍቱ ከተማ በተካኼደበት መድረክ ላይ በመጀመሪያዎቹ 6 ወራት 640 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 709 ቢሊየን ብር መሰብሰብ እንደተቻለ አመልክተዋል።
በዚህም ከዕቅዱ አንጻር ከ110 በመቶ በላይ መሳካቱን አንስተው÷ የጥር ወር ሲጨመር 760 ቢሊየን ብር እስካሁን መሰብሰብ መቻሉ ይፋ ኾኗል።
ከተሰበሰበው ገቢ ውስጥም የሀገር ውስጥ 366 ቢሊየን ብር እንዲሁም ከቀረጥና ታክስ 342 ቢሊየን ብር ድርሻ እንዳላቸው አብራርተዋል።
የገቢዎች ሚኒስትር አይናለም ንጉሴ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ከሌሎች ሀገራት ጋር ተመሳሳይ ገቢ የመሰብሰብ አቅም እንዲኖር ለማስቻል የገቢ ስትራቴጂ ተነድፎ ወደ ስራ ተገብቷል።
