ጊቤ ሦስት የኃይል ማመንጫ ግድብ 3 ሺህ 210 ቶን ዓሣ ተመረተ

Date:

በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት የጊቤ ሦስት የኃይል ማመንጫ ግድብ በፈጠረው ሰው ሰራሽ ሐይቅ 3 ሺህ 210 ቶን የዓሣ ምርት ተገኘ።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የዳውሮ ዞን ግብርና መምሪያ የእንስሳትና ዓሣ ሃብት ልማት ዘርፍ ኃላፊ አስፋው ጮራሞ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት፤ በዞኑ ከኩሬ እና ከተለያዩ ውሃ አካላት 4 ሺህ 200 ቶን የዓሣ ስጋ ለማምረት ታቅዶ 4 ሺህ 111 ነጥብ 6 ቶን ዓሳ ተመርቷል።

ከዚህ ውስጥ 3 ሺህ 210 ቶን ምርት የተገኘው የጊቤ ሦስት የኃይል ማመንጫ ግድብ ከፈጠረው ሰው ሰራሽ ሐይቅ ነው ብለዋል።

በሐይቁ ላይ 160 ወጣቶች በተለያዩ ማህበራት ተደራጅተው በዓሣ ማምረት ስራ ላይ የተሰማሩ መሆኑን ተናግረዋል።

ለወጣቶቹ ምርታማነታቸው እንዲጨምር የሚያስችል ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሆነ ጠቅሰው የምርት ማከማቻና መሸጫ ሼድ ግንባታ፣ የምርት ማቆያ ፍሪጆች እና ሐይቅ ላይ የምርት ማጓጓዣ የሞተር ጀልባ እንዲያገኙ ተደርጓል ነው ያሉት።

እንዲሁም ምርትን ወደ ተለያዩ የአካባቢ ገበያዎች አጓጉዘው የሚሸጡበት ፍሪጅ የተገጠመለት መኪና እና ሌሎች ድጋፍ መደረጋቸውን ገልጸዋል።

ወጣቶቹ በቀን እስከ አንድ ቶን የሚደርስ ዓሣ እያመረቱ መሆናቸውን ገልጸው ከአካባቢ ገበያ ጀምሮ እስከ ማዕከላዊ ገበያ ድረስ ምርት እያቀረቡ እንደሚገኙ አስረድተዋል።

የጊቤ ሦስት የኃይል ማመንጫ ግድብ 1 ሺህ 870 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ በማመንጨት ከታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ቀጥሎ ግዙፉ የኃይል ማመንጫ ሲሆን÷ ግድቡን ተከትሎ የተገነባው የሀላላ ሎጅም ለአካባቢው የቱሪስት መዳረሻ በመሆን የገቢ ምንጭ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል።

(ኤፍ ኤም ሲ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...