ጋዜጠኛ ሳልሳዊት ባይነሳኝ መፈታቷን ተረጋገጠ

Date:

የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ድርጅት (CPJ) የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ጋዜጠኛዋን  በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቁ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጠይቆ ነበር ።

የጋዜጠኛዋ ታናሽ እህት ኃይማኖት ባይነሳኝ እንዳሉት ሳልሳዊት ከ13 ቀናት እስር በኋላ ዛሬ ከሰዓት በኋላ አስር ሰዓት አካባቢ ከእስር ተለቃለች።

ጋዜጠኛ ሳልሳዊት ባለፈው ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ/ም  ከተከናወነው ምርጫ ማግስት በኦሮሚያ ክልል ስለደረሰው ጥቃት  በማህበራዊ መገናኛ ገጾቿ ላይ በመተቸቷ  ሰኔ 1 ቀን 2018 ዓ/ም አዲስ አበባ ውስጥ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቷ ተወስዳ መታሰሯን ቤተሰቦቿ ገልጸው ነበር።

የሲፒጄ  የአፍሪካ ዳይሬክተር አንጄላ ኩዊንታል ጋዜጠኛዋ ያለ ምንም ክስ ፍርድ ቤት ሳትቀርብ በእስር ላይ እንድትቆይ መደረጉ «የሰብአዊ መብት ጥሰት ነው» ማለታቸውን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።

የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ጋዜጠኛዋን በአስቸኳይ እንዲፈቱ ወይም ክሷን በግልጽ አሳውቀው ፍርድ ቤት እንዲያቀርቧት ድርጅቱ ጥሪ አቅርቦ ነበር።

ቀደም ሲል በመንግስት መገናኛ ብዙሃን ትሰራ የነበረችው ሳልሳዊት፣ በገለልተኛ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የምታቀርበው ትችት ለመታሰሯ ምክንያት ሳይሆን እንዳልቀረ ይታመናል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በቬንዝዌላ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ የ32 ሰዎች ህይወት አልፏል

በቬንዙዌላ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀ ሲሆን 7.2 እና 7.5...

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ “ሉሲ” ላገኟት ፕሮፌሰር የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጠ

የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ፥...

የሳህለወርቅ ዘውዴ አዲሱ አለም አቀፍ ሹመት በተመድ ልዩ ተልእኮ ተሰጣቸው

የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ወይዘሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ በተመድ ዋና ፀሀፊ...

በሳዑዲ በምሕረት የተለቀቁ 320 ኢትዮጵያውያን

በሳዑዲ አረቢያ የፍርድ ሂደታቸው ተቋርጦ የምህረት አዋጅ ከተሰጣቸው 1...