ጌጅ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በ2017 የትምህርት ዘመን በቀንና በማታ ያስተማራቸው ተማሪዎችን ማስመረቁን አስታውቋል ።
ጌጅ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በመማር ማስተማር ከፍተኛ ልምድ ያለው የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ሲሆን በመጀመሪያ ዲግሪና በቴክኒክና ሙያ ስልጠና የመግቢያ መስፈርቱን ያሟሉ ተማሪዎችን በማስተማር ነሐሴ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ማስመረቁን ሰምተናል።
ዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ አጠቃላይ 2465 ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሆን የመጀመሪያ ዲግሪ በቀና በማታ የትምህርት መርሀግብር እንዲሁም በቴክኒክና ሙያ የትምህርት ዘርፎች በአዲስአበባ ዩኒቨርስቲ 6 ኪሎ ካምፓስ ጊቢ ውስጥ ማስመረቁ አስታውቋል።
በምረቃ መርሃግብሩ፣ በትምህርት ሚኒስቴር የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አገለግሎት ኃላፊን ጨምሮ የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ስራ አስኪያጅ በተገኙበት የተከናወነ ሲሆን ለተመራቂዎች የሕይወት ልምድ መልእክት በማስተላለፍ መከናወኑን ታውቋል።
ጌጅ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ በትምህርት ዘርፍ ከተሰማሩ ከፍተኛ የትምህርት መስጫ ተቋማት እድሜ ጠገብ ከሚባሉት ተርታ የሚመደቡ መካከል አንዱ ሲሆን የመማር ማስተማር አገልግሎት መስጠት ከጀመረ 23 አመታት ያስቆጠረ ተቋም መሆኑን ከኮሌጁ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
በአዲሱ በጀት አመት አዳዲስ የትምህርት አይነቶች ለመጨመር ውጥን እንዳለው የተገለፀ ሲሆን ከተለያዩ አለማቀፍ የትምህርት ተቋማት ጋር በመተባበር ሁለተኛ እና ሶስተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች በትብብር ለመስራት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ዩኒቨርስቲ ኮሌጁ ገልጿል ።
በተጨማሪም በበይነመረብ የትምህርት አገልግሎት ለመስጠት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየሰራ መሆኑንና ፍቃድ ለማግኘትም በብርቱ እየሰራ እንደሚገኝ የትምህርት ተቋሙ በመረሀግብሩ ላይ አስታውቋል።
ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን እንዲሁም ከአዲስ አበባ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን የሚሰጠውን እውቅና ፈቃድ በመውሰድ በአዲስአበባ የተለያዩ አካባቢዎች ቅርንጫፎች ከፍቶ እየሰራ እንደሚገኝ ከዩኒቨርስቲ ኮሌጁ ያገኘነውን መግለጫ ላይ ተመልክተናል።
በቀጣይ የ2018 ዓ.ም.የትምህርት አዲስ ዓመት ዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ በዋነኛነት ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራባቸው፡-
❖ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ አዳዲስ ፕሮግራሞች ለመክፈት ጥረት የሚያድግበት
❖ 2ኛ እና 3ኛ ድግሪ ፕሮግራም ከዓለም አቀፍ ዩኒቨርስቲዎች ጋር በጋራ ለመስራት እቅድ ይዘዋል።
❖ ጥራት ያለው አገልግሎትና ትምህርት ለተማሪዎች በሁሉም ካምፓሶች በወጥነት መስጠቱን አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንም ገልፀዋል ።
❖ የኦላይን የትምህርት ፈቃድ ለማግኘት ስራወች እየተሰሩ ነዉም ብለዋል።
❖ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ ሲስተሞች በተሻለ ሁኔታ አገልግሎት የሚሰጡበትን ሁኔታም ማመቻቸታቸዉም ሰምተናል።
