ግብር ከፋዮች የሚያቀርቡት ቅሬታ በየሳምንቱ ሐሙስ ይደመጣል

Date:

ከአዲስ አበባ የግብር አሰባሰብና የገቢዎች አገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ የሚኖረውን ማንኛውም አይነት ቅሬታ መፍታት የሚያስችል አዲስ አሰራር በከንቲባ ፅ/ቤት ሥር መዋቀሩ ተገልጿል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የገቢዎች ቢሮ ሥር የተዘረጋው የቅሬታ አፈታት ስርዓት እንደተጠበቀ ሆኖ በዚያ ያልረካ ግብር ከፋይ ከንቲባ ፅ/ቤት ማንኛዉንም አይነት ከገቢ አሰባሰብ፣ ከሠራተኞች ሥነ-ምግባር እና አገልግሎት አሰጣጥ ጋር የሚነሱ የግብር ከፋዮች ቅሬታዎችን ለመፍታት ዘወትር ሐሙስ ኃላፊዎች በተገኙበት የሚደመጥ እና ተጣርቶ ምላሽ የሚሰጥበትን አሰራር መዘርጋቱን ነው የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ፅ/ቤት ያስታወቀው።

በዚህም መሠረት በሚስጥር ጥቆማ የሚሰጥበትን ነፃ የጥሪ ማዕከል 9977 ፣ የሚስጥር ሳጥንን ጨምሮ በተጨባጭ ቅሬታዉን በአካል ለበላይ አመራር ማቅረብ የሚችልበትን አሰራር ወደ ተግባር ይገባል ተብሏል።

በመሆኑም ከመጪው ሐሙስ ሕዳር 25 ቀን 2018 ጀምሮ ጠዋት ከ 2 ሰዓት እስከ 7 ሰአት ድረስ ከገቢዎች ጋር ብቻ የተያያዘን ቅሬታ አመራሩ ተቀብሎ የሚስተናግድ መሆኑን በመረዳት፤ በከንቲባ ፅ/ቤት ተጨባጭ ቅሬታ ያላቸው ግብር ከፋዮቭ ማቅረብ የሚችሉ መሆኑን የከተማው አስተዳደር አስታውቋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...

ትራምፕ ኢራን ላይ ያላቸው ትዕግሥት እየተሟጠጠ መሆኑን ተናገሩ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው መሪ ዢ ጂንፒንግ ጋር...