ግብፆች በዓባይ ጉዳይ 560 ስብሰባዎችን አካሂደው እንደነበር ተገለጸ

Date:

ግብፆች በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ የዓለም ሀገራትን ከጎናቸው ለማሰለፍ እና በኢትዮጵያ ላይ እርምጃ ለመውሰድ 560 ስብሰባዎችን አካሂደው እንደነበር በዓባይ እና በኢትዮጵያ ጉዳይ በተለያዩ መድረኮች ሲሟገቱ የሚታወቁት የታሪክ ምሁር እና ተመራማሪው ፕሮፌሰር አደም ካሚል ገለጹ። ግብፅ ግድቡን ለመምታት ራፋል የተባለ የጦር አውሮፕላን ገዝታ እንደነበርም ፕሮፌሰሩ ተናግረዋል።

ከበኩር ጋዜጣ የመስከረም 12 ቀን 2018 ዓ.ም እትም እንግዳ አምድ ጋር ቆይታ ያደረጉት የታሪክ ምሁሩና ተመራማሪው ፕሮፌሰር አደም ካሚል፤ “ከጥንት ጀምሮ የግብፅ መሪዎች ኢትዮጵያ ጠንካራ እንዳትሆን እንዲሁም አንድነት እንዳይኖራት ያላደረጉት ጥረት ያልፈፀሙትም ሴራ የለም” ብለዋል።

በተለይም ከዓባይ ወንዝ ጋር በተያያዘ ከገማል አብደላ ናስር እስከ አንዋር ሳዳት፣ ከሙሀመድ ሙርሲ እስከ አብዱልፈታህ አልሲሲ ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ ግድብ እንዳትሰራ “ኢትዮጵያን እናጠፋለን” የሚል ዛቻ እስከመሰንዘር የደረሰ እንደነበር አመላክተዋል።

በዚህም ግብፆች በህዳሴው ግድብ ዙሪያ የዓለም ሀገራትን ከጎናቸው ለማሰለፍ እና በኢትዮጵያ ላይ እርምጃ ለመውሰድ 560 ጊዜ ስብሰባዎችን አድርገዋል። 1850 ጊዜ በኢትዮጵያ ግድብ ላይ ሴራን የሚጠነስሱ ሴሚናሮችን አካሂደዋል። ሙሉውን ዜና ፌስቡክ ገጻችን ላይ ያገኙታል።

አዲስ_ማለዳ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...