ጎዶ ስማርት ሪልስቴት ለቤት ፈላጊዎች የዋጋ ቅናሽ ማድረጉን ገለጸ

Date:

በአፍሪካ ሆልዲንግ ግሩፕ ስር ከሚገኙ ድርጅቶች አንዱ የሆነው ጎዶ ስማርት ሪልስቴት፣ በአሁኑ ወቅት እየተስተዋለ የሚገኘውን የኑሮ ውድነት ምክንያት በማድረግ፣ ለቤት ፈላጊዎች የዋጋ ቅናሽ ማድረጉን ገልጿል። የዋጋ ቅናሹ የተደረገው በቅድሚያ 25 በመቶውን ለሚከፍሉ የቤት ፈላጊዎች ነው፡፡

የአፍሪካ ሆልዲንግ ግሩፕ ባለራዕይ እና ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ደረጀ ማሙዬ፣ ከዚህ በፊት አንድ ቤት በካሬ 75 ሺሕ ብር ሲሸጥ መቆየቱን አውስተው፣ ነገር ግን አሁን በአገሪቱ ባለው የኑሮ ወድነት ምክንያት እስከ ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም. የሚቆይ የዋጋ ቅናሽ ተደርጓል። በመሆኑም አንድ ቤት በካሬ 67 ሺሕ 500 ብር እየተሸጠ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

ይህ የዋጋ ቅናሽ የተደረገው በቅድሚያ 25 በመቶ ለሚከፍሉ የቤት ፈላጊዎች መሆኑን ያመለከቱት አቶ ደረጀ፤ የመኖሪያ ቤቶቹ ሕንጻ ግንባታ የሚከናወነው በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል አካባቢ፣ በተለምዶ “ሜዳ ጋራዥ” ተብሎ በሚጠራው ቦታ መሆኑን አብራርተዋል። “በ10 ሺሕ ካሬሜትር (1 ሄክታር) መሬት ላይ ያረፈው ይህ ሕንጻ፣ እስከ 35 ወለል ያለው ሲሆን፣  ከ1 እስከ 4 መኝታ ክፍሎች ያሉት አፓርታማዎችን ያቀፈ ፕሮጀክት ነው” ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ የግንባታው ቦታ ከ10 እስከ 200 ካሬሜትር የሚለያዩ ‘ዩኒቶች’ ያሉት “አፍሪካን ቢዝነስ ሴንተር” የተባለ የገበያ ማዕከል ማካተቱን አቶ ደረጀ አያይዘው ገልጸዋል። ይህም የአካባቢውን የንግድ ዕንቅስቃሴ በማበረታታት ለነዋሪዎቹ የዕለት ተዕለት ምቹ ሁኔታዎችን ለማቅረብ በማለም እንደሆነ ነው ያስረዱት።

ይህ የግንባታ ፕሮጀክት በአጠቃላይ 15 ቢሊዮን ብር እንደሚፈጅ አቶ ደረጀ አስታውቀው፣ በሱሉልታ ከተማ ደግሞ የግንባታ ግብዓት ማምረቻ ለማቋቋም የተለያዩ ስራዎች በተቋማቸው እየተሰሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

ጎዶ ሪልስቴት ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠር መቻሉን ዋና ስራ አስፈጻሚው ትናንት ግንቦት 28 ቀን 2017 ዓ.ም. በጽሕፈት ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ያረጋገጡ ሲሆን፣ ድርጅታቸው በ10 ዓመት ጊዜ ውስጥ 500 ሺሕ ቤቶችን የመስራት ዕቅድ እንዳለው ተናግረዋል፡፡

አፍሪካ ሆልዲንግ ግሩፕ በ2013 ዓ.ም. የተቋቋመ አገር በቀል ድርጅት ሲሆን፣ ጎዶ ስማርት ሪልስቴት፣ ኮዴኮ ካፌ፣ ቡዴና አዮ፣ አጋ አካዳሚ፣ የአፍሪካ የንግድ ማዕከል እና ኦሺን ቴክኖሎጂ በኩባንያው ስር የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ናቸው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...