ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለይፋዊ ጉብኝት አዘርባጃን ገቡ

Date:

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለይፋዊ ጉብኝት አዘርባጃን ዋና ከተማ ባኩ መግባታቸውን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ።

የአዘርባጀን መንግሥት የዜና ወኪል የሆነው ‘አዛርታክ’፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሐሙስ የካቲት 19/2018 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ በአህጉረ እስያ እና አውሮፓ ወደ ምትገኘው አገር መድረሳቸውን ዘግቧል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጽህፈት ቤት ምሽት ላይ ጉብኝቱን በማስመልከት በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ባሰፈረው መልዕክት እና ምሥል አስታውቋል።

በዚህም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና ከከፍተኛ የልዑካን ቡድናቸው ጋር ሐሙስ ረፋድ ላይ አዘርባጃን መግባታቸውን አመለክቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ባኩ ውስጥ በሚገኘው ሃይደር አሊየቭ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የአገሪቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሳሚር ሻሪፎቭ እና ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያልቺን ራፊየቭ እንዲሁም ሌሎች ባለሥልጣናት ተገኝተው አቀባበል እንዳደረጉላቸው ዘካስፒያን ፖስት እና ሪፖርት የተባሉት የአገሪቱ የዜና ድረገጾች ዘግበዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ይፋዊ ጉብኝት ለምን ያህል ቀናት እንደሚደረግ፣ ከየትኞቹ የአገሪቱ ባለሥልጣናት ጋር እንደሚገናኙ እና በምን ጉዳይ እንደሚነጋገሩ በይፋ አልተገለጸም።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት በኢትዮጵያ እና በአዘርባጃን መካከል ያለው ግንኙነት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እየጠነከረ መምጣቱን እና ለዚህም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸው መሳያ መሆነት ጠቅሷል።

በአሁኑ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና የልዑካቸው ጉብኝት የአገራቱን የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን ወደ ላቀ እና ትርጉም ወዳለው ደረጃ እንደሚያደርስ ይጠበቃል ብሏል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በካስፒያን ባሕር እና በካውካሰስ ተራሮች መካከል በአውሮፓን እና በእስያ አዋሳኝ ቦታ ላይ ወደምትገኘው የቀድሞዋ ሶቪየት ኅብረት አካል አዘርባጃን፤ ያደረጉት ጉዞን በተመለከተ በራሳቸውም ሆነ በጽህፈት ቤታቸው በኩል እስካሁን የተገለጸ ነገር የለም።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...