ፀሐይ መማር ትወዳለች ቅርጫፍ ተከፈተላት

Date:

የእናት ባንክ በማህበረሰብ ሥራ ፈጣሪ ወይዘሮ ብሩክታዊት ጥጋቡ ስም የሰየመችው፣ አዲስ አበባ ከተማ ሲዳማ ተራ ቅርንጫፍ ተመርቋል።

እናት ባንክ በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ በተለየ መልኩ የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ አቅም ለማጎልበትና ለሁሉም ህብረተሰብ የተሟላ የባንክ አገልግሎት ለመስጠት በባለርዕይ ሴቶች የተቋቋመች ባንክ ስትሆን፤ ለዚህም በመላው ሀገሪቱ  208 ቅርንጫፎችን በመክፈትና በዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት እየሰጠች ትገኛለች፡፡

በዛሬው ዕለት ቅርንጫፉ የእናት ባንክ  ከፍተኛ አመራሮች፣ሰራተኞችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በደማቅ ሥነ-ስርዓት ተመርቋል።

“የዚች አገር እውነት ያለው እናቶች ጋር ነው” ወ/ሮ ብሩክታዊት ጥጋቡ

የታዋቂዉ ፀሐይ መማር ትወዳለች የልጆች ፕሮግራም አዘጋጅ ፤ የዊዝኪድስ ዎርክሾፕ መሥራች እና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ብሩክታዊት ጥጋቡ ይህንን የተናገሩት እናት ባንክ በሥማቸው በከፈተው አዲስ ቅርንጫፍ መክፈቻ ፕሮግራም ላይ ነው።

እናት ባንክ በመርካቶ ሲዳሞ ተራ በወ/ሮ ብሩክታዊት ጥጋቡ ሥም የተሰየመውን አዲስ ቅርንጫፉን  በዛሬው ዕለት ቅዳሜ 16/09/2017 ዓ.ም ከፍቷል።

እናት ባንክ  የነገ ፍሬ ለሆኑ ህፃናት በእናትነት ሥነ ልቦና ብሩክታዊት ጥጋቡ በወርክሾፓቸው እየሠሩት ስላለው ሥራ ያበረከተው ሽልማት መሆኑንም አስታውቋል።

ወ/ሮ ብሩክታዊት ጥጋቡ በበኩላቸው የልጆችን መፃዒ እድል በመወሰን ረገድ እናቶች እውነተኛዎቹ ማሕበረሰብ አቅኚዎች ናቸው ያሉ ሲሆን ልጆች ላይ መሥራት አገር መገንባት እንደሆነ ተናግረዋል።

እናት ባንክ በሥማቸው ስለከፈተው ቅርንጫፍም የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...