«ፍትህ በግፍ እየሞቱ ላሉ እና ትኩረት ለተነፈጋቸው ንፁሀን ወገኖቻችን»

Date:

የአክብሮት ሰላምታዬን በማስቀደም ለመላው ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን በሙሉ እንኳን ለታሪካዊውና አንጸባራቂው የአድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ የሚል መልዕክቴን ሳስተላልፍ በታላቅ ብሄራዊ ኩራት ነው፡፡

የዘንድሮውን ፻፴ ኛው የአድዋ ድል በዓል ስናከብር ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሀገራችን ባለው የፖለቲካ አለመረጋጋት ሳቢያ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች እስካሁኗ ሰዓት ድረስ በማንነታቸው ብቻ ተለይተው እጅግ ኢ-ሰብዓዊ በሆነ መንገድ በአሰቃቂ ሁኔታ በግፍ እየተገደሉ ያሉ

እንዲሁም የአካል እና የስነልቦና ጕዳት የሚደርስባቸው ብሎም ከቤት ንብረታቸው ከቀያቸው የሚፈናቀሉ ንፁሀን ወገኖቻችንን በህሊና ፀሎት እያሰብን እና ለዚህም እየተባባሰ ለመጣው ትኩረትም ለተነፈገው ማህበራዊና ሀገራዊ ቀውስ መንስኤው ሀገራችን ኢትዮጵያን ላለፏት ቀላል ለማይባሉ አመታት ቁልቁል ሰብቆ የያዛት የዘር ፖለቲካ መሆኑን አፅንኦት በመስጠት

ከመቼውም ጊዜ በላቀ መላው ኢትዮጵያውያን ዘር ሀይማኖት ሳንለይ በአንድነት በመቆም ለጋራ ህልውናችን ስጋት የሆነውን ጎሳን መሰረት ያደረገ ስርዓት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በቃ ልንለው የሚገባ መሆኑን በጥብቅ በማሳሰብም ጭምር ነው።

«ፍትህ በግፍ እየሞቱ ላሉ እና ትኩረት ለተነፈፖ ንፁሀን ወገኖቻችን»

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር! ፍቅር ያሸንፍል!

ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...