ፕሬዝዳንት ትራምፕ በሆርሙዝ ሰርጥ ጉዳይ ለማገዝ ጉጉት አልታየባቸውም ያሏቸውን አገራት ወቀሱ

Date:




የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን በተዘጋው የሆርሙዝ ሰርጥ በኩል የሚያልፈውን ነዳጅ ለማጀብ የጦር መርከቦቻቸውን እንዲልኩ ያቀረቡትን ጥያቄ ውድቅ ያደረጉን ምዕራባውያን አጋሮቻቸውን በምስጋና ቢስነት ወቀሱ።

Aትራምፕ ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደ ዩናይትድ ኪንግደም እና የኔቶ አባላት ያሉ አጋሮች በጦርነቱ ከአሜሪካ ጋር ለመሰለፍ አንገራግረዋል ሲሉ ተችተዋል። በተለይም ዩናይትድ ኪንግደም ጦርነቱን በተመለከተ ባሳየችው አቋም “እጅግ መገረማቸውን” ተናግረዋል።


ትራምፕ፤ “ከሁለት ሳምንት በፊት ‘ለምን ተጨማሪ መርከቦችን አትልኩም’ አልኩ። [የዩኬ ጠቅላይ ሚኒስትር] እውነትም ማድረግ አልፈለገም ነበር” ሲሉ የዩናይትድ ኪንግደሙን መሪ ኪር ስታርመር ወቅሰዋል።


“አካባቢው ላይ ፈንጂ የሚቀርብ መርከብ እንዳላቸው ይነግሩናል፤ ማድረግ ግን አይፈልጉም፤ ይሄ መጥፎ ነው” ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ በዩናይትድ ኪንግደም “ደስተኛ አይደለሁም” ሲሉም ተደምጠዋል። “ሊሳተፉ እንደሚችሉ አስባለሁ፤ ነገር ግን በጉጉት መሳተፍ አለባቸው” ብለዋል።


በአሜሪካ እና እስራኤል ጦርነት የተከፈተባት ኢራን ከዓለም ነዳጅ 20 በመቶ ገደማው የሚተላለፍበትን የሆርሙዝ ሰርጥን ዘግታለች። ሊያልፉ የሞከሩ መርከቦች ላይም ጥቃት ተፈጽሟል።


ወሳኙ መተላለፊያ እንዲከፈት የሚደረገውን ጥረት ቢያንስ አምስት አገራት ይቀላቀላሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ትራምፕ ተናግረው ነበር። ጀርመን፣ ስፔን እና ጣልያንን ጨምሮ በርካታ የአሜሪካ አጋር አገራት አሁን ወደ ሰርጡ የጦር መርከብ የመላክ እቅድ እንደሌላቸው ተናግረዋል።


ትራምፕ ትናንት በዋይት ሀውስ ባደረጉት ንግግር አገራት እገዛ ለማድረግ መንገድ ላይ ናቸው ሲሉ ተደምጠዋል። የትኛዎቹ አገራት ድጋፍ እንደሚደርጉ ባይጠቅሱም፤ በቅርቡ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ይገልጻል ብለዋል።
“የተወሰኑ አገራት [እገዛ ለማድረግ] ጉጉት አላቸው፤ የተወሰኑት ደግሞ የላቸውም” ሲሉ ተናግረዋል። “አንዳንድ አገራትን ለብዙ፣ ብዙ ዓመታት አግዘናቸዋል፤ ከመጥፎ የውጪ አካል ጠብቀናቸዋል፤ እናም ግን [እኛን ለማገዝ] ጉጉት አልነበራቸውም። ምን ያህል ጓጉተዋል የሚለው ለእኔ ዋጋ አለው” ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...