100 ተቋማት የንብረት ምዝገባ እንዲያካሂዱ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ አስተላለፈ

Date:

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችን የሚከታተለውና የሚቆጣጠረው ባለሥልጣን፣ በሲቪል ማኅበራት ዘርፍ ለሚንቀሳቀሱ 100 ተቋማት የንብረት ምዝገባ እንዲያካሂዱ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ አስተላለፈ። ከእነዚህም መካከል 70 የሚሆኑት የውጭ ድርጅቶች ይገኙበታል። ድርጅቶቹ ንብረታቸውን መዝግበው እንዲልኩ የተሰጠው ቀነ ገደብ እስከ ህዳር 13 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ነው።

ባለሥልጣኑ ለድርጅቶቹ በላከው ደብዳቤ ላይ እንዳስረዳው፣ የንብረት ምዝገባው የሲቪል ማኅበራት በሕግ የተሰጣቸውን የንብረት ባለቤትነት መብት ሳይነካ፣ የሕዝብ ሀብት አጠቃቀም ማረጋገጫ እና  የዘርፉን አጠቃላይ መረጃ ማጠናቀር የሚሉት ዓላማዎችን ለማሳካት ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል።

በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 መሰረት፣ በሕዝብ ስም የተሰበሰበው ሀብት ለታለመለት የሕዝብ ዓላማ መዋሉን የማረጋገጥ ግዴታ በባለሥልጣኑ ላይ የሚጣል ሲሆን፣ ይህንን ግዴታ ለመወጣት የንብረት ምዝገባው ወሳኝ መሆኑን አስረድቷል።

በአገር ደረጃ በሲቪል ማኅበረሰብ ዘርፍ ስር ምን ያህል የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ ንብረት እንዳለ ጥቅል መረጃ ለመያዝ፣ ለመሰብሰብና ለማጠናቀር የምዝገባው ሂደት እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።

capital news

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...