100 ኢትዮጵያውያን ነፃ የውጭ የትምህርት ዕድል ማግኘታቸውን የእስራኤል ኤምባሲ ገለጸ

Date:

የኢትዮጵያና እስራኤል የትብብር መስኮች ውስጥ አንዱ በሆነው የትምህርት ዕድል፣ በዚህ ዓመት 100 ተማሪዎች በመንግስት ለመንግስት በሚደረገው ግንኙነት ወደ እስራኤል ለትምህርት ማቅናታቸውን የእስራኤል ኤምባሲ ለአሐዱ ገልጿል።

በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አብረሃም ንጉሴ፤ ተማሪዎቹ በተለያየ መስክ ሙያ ሰልጥነውና ልምድን ቀስመው የሚመለሱባቸው ሁኔታዎች መኖራቸውን ገልጸዋል።

ከእነዚህም መካከል በመንግስት ለመንግስት በሚደረገው ግንኙነት፣ በእስራኤል የውጭ ግንኙነት ማዕቀፍ ውስጥ የሚሰጠው የትምህርት ዕድል አንዱ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በግብርና፣ ቴክኖሎጂ፣ ህክምና እንዲሁም በሰላምና ፀጥታ ዘርፎች የረጅም እና የአጭር ጊዜ ስልጠናዎች እየተሰጡ መሆናቸውን የገለጹት አምባሳደሩ፤ ስልጠናው የሴቶች የአመራር ክህሎት እና የህፃናት ዕድገትንም የሚያካትት መሆኑን ጠቁመዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በግሉ ዘርፍ በሚደረግ ግንኙነት ባለሙያዎችን በተለያየ መንገድ በማሰልጠን ወደ ስራ የሚያስገቡበት ሁኔታ መኖሩን አንስተዋል።

ለአብነትም “Save a Child’s Heart” የተባለው ድርጅት በእስራኤል ሀገር ለአምስት ዓመታት ለአምስት የህክምና ባለሙያዎች የትምህርት ዕድል በመስጠት፣ አሁን ላይ በኢትዮጵያ በስፔሻሊስትነት ደረጃ እየሰሩ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ጉምሩክ ኮሚሽን ከአንድ ትሪሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ማቀዱን ገለጸ

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን በ2018 በጀት ዓመት 725.25 ቢሊዮን ብር...

ከ1.5 ሚሊዮን ዶላር የአፍሪካ ንፁህ ኢነርጂ ፈንድ አምስቱ አቅኚ የኢትዮጵያ ድርጅቶች ተመረጡ

በምስራቅ አፍሪካ የንፁህ ኢነርጂ አቅርቦትን በማሳደግ የስራ እድልን ለመፍጠርና...

ታላቅ የምስጋና እና የስጦታ መርሃ-ግብር ጥሪ!

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ባለፉት 5 ዓመታት ላበረከቱት ከፍተኛና ታላቅ...

የቀድሞዉ የኢራን ላዕላይ መሪ አያቶላሕ ዓሊ ኻምኔይ ተቀበሩ

ዩናይትድ ስቴትስና እስራኤል ባለፈዉ የካቲት ማብቂያ ላይ የገደሏቸዉ የኢራን...