180 የእስራኤል ኢንቨስተሮች በኢትዮጵያ በግብርና እና ቴክኖሎጂ ዘርፎች እየተሳተፉ ነዉ

Date:



👉ጤፍን ከኢትዮጵያ ከሚረከቡ ሐገራት መካከል እስራኤል ዋነኛዋ ነች ተ

በኢትዮጵያ 180 የሚሆኑ የእስራኤል ባለሀብቶች በግብርና፣ በቴክኖሎጂ እና በማዕድን ዘርፎች ተሰማርተው በስራ ላይ እንደሚገኙ በኢትዮጵያ የእስራኤል ኤምባሲ አስታውቋል።

ከባለሀብቶቹ መካከል በግብርናው ዘርፍ የተሰማሩት ኢንቨስተሮች በደብረ ዘይት እና በአካባቢዋ የጠብታ መስኖን በመጠቀም ዘመናዊ እርሻ ላይ የተሰማሩ እንደሚገኙበት ተገልጿል።

የዶሮ እርባታ እና የአሳ ልማት ስራዎችም እስራኤላውያኑ ባለሐብቶች እየተንቀሳቀሱባቸው ካሉ የኢንቨስትመንት ዘርፎች መካከል ይገኙበታል።

በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አቭራሃም ንጉሤ እንደገለጹት፣ የሁለቱ ሀገራት የንግድ ማኅበረሰብ በኢንቨስትመንት እና በቱሪዝም ዘርፍ ያላቸው ትብብር እየተጠናከረ ነው።

ኤምባሲው የኢትዮጵያን ወቅታዊ የኢንቨስትመንት መረጃዎች ለእስራኤል ለባለሀብቶች የማድረስ ስራ እየሰራ መሆኑንም አምባሳደሩ አስታውሰዋል።

ኢትዮጵያ በበኩሏ ከፍተኛ መጠን ያለው ጤፍ፣ ቡና እና ሰሊጥ ወደ እስራኤል እንደምትልክ ተጠቅሷል።

በእስራኤል የሚኖሩ 180 ሺህ ቤተ-እስራኤላውያን የኢትዮጵያ ጤፍ ዋነኛ ተጠቃሚ ሲሆኑ፤ በምላሹ ከእስራኤል ወደ ኢትዮጵያ ደግሞ የቴክኖሎጂ ምርቶች እና የጤና መሳሪያዎች በብዛት እንደሚገቡ ተገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች  565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት...

የአማርኛ ቋንቋ እውነተኛ ምንጭ ቤተ መንግሥት ሳይሆን ሕዝብና ሠራዊት ነው

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም አዘጋጅነት ከስድስት...

አዲስ አበባ፦ የዜጎች ቀይ መስመር!

(የግል አስተያየት) አዲስ አበባ የኢትዮጵያውያን መናገሻ፣ የበርካታ ብሔረሰቦች ባህሎች ለዘመናት...

አብን የምክክሩን ውጤት ውድቅ አደረገ!

አብን በሀገራዊ ምክክሩ ማጠቃለያ ላይ የተፈጸመውን “ሕገ-ወጥ ጣልቃ-ገብነት” በመቃወም...