2018 ዓ.ም ሁሉም ተማሪ ዩኒቨርስቲ የሚገባበት ቀን ተወሰነ

Date:

መስከረም 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የቀጣዩ አመት የዩኒቨርስቲ ት/ት ይጀመራል ሲል ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የፈተና ውጤት ጳጉሜ ላይ ይፋ ይሆናል በማለት እስከዚያም ድረስ የሚቆየው ፈተና ያልወሰዱና በመጪው ነሐሴ ወር ለፈተና የሚቀመጡ ቀሪ ተፈታኝ ተማሪዎች በመኖራቸው መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።

በተለያየ ምክንያት ዘግይተው ትምህርት የጀመሩ በመኖራቸው ነው ፈተና እኩል ያልወሰዱ ተፈታኞች ያሉት በማለትም በመሆኑም ጳጉሜ ወር ላይ የ12ኛ ክፍል የፈተና ውጤት ከታወቀ በኋላ መስከረም 8 ቀን ሁሉም ተማሪ ዩኒቨርስቲ የሚጀምርበት እለት እንደሚሆን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

የትምህርት ካላንደርን በአግባቡ አክብሮ በመስራት የፈተና ጊዜያትንም ላለመሻማት ይሰራል ሲሉ ያከሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ከመስከረም ጀምሮ ጥብቅ አሰራር እንደሚኖር ገልጸዋል።

እንደ ሀገር እኩል ውጤት ተናግሮ በእኩል ትምህርት ለማስጀመር ሲባል ቀሪ ያልተፈተኑ ተፈታኝ ተማሪዎችን ጠብቆ ማስጨረስ እንደሚገባ የተናገሩት የትምህርት ሚኒስትሩ በራሳቸው ፈቃድና ምክንያት አስቀድመው ፈተና ላይ ካልተቀመጡት በቀር ሌሎቹ የመመዘኛ መስፈርቱ አካል መሆናቸውን ገልጸዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በመንገድ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ

አደጋው የደረሰው ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ...

ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች  565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት...

የአማርኛ ቋንቋ እውነተኛ ምንጭ ቤተ መንግሥት ሳይሆን ሕዝብና ሠራዊት ነው

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም አዘጋጅነት ከስድስት...