ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ ልታካሂድ ነው

Date:

ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ መላ አገሪቱን የሚያዳርስ የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ ለማካሄድ ዝግጅት እያደረገች ነው። የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በ2018 ዓ.ም. ለሚካሄደው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ የቅድመ ዝግጅት ሥራ መጀመሩን ይፋ አድርጓል።

ይህ ቆጠራ ከመስከረም ወር ጀምሮ በመላው አገሪቱ ከትናንሽ እስከ ትላልቅ የምርትና የንግድ ድርጅቶች ላይ የሚካሄድ በመሆኑ፣ በየደረጃው ያለው የመንግሥት አደረጃጀት፣ የኢኮኖሚ ድርጅት ባለቤቶች እንዲዘጋጁ ተጠይቋል።

የቅድመ ዝግጅት ተግባራት የቆጠራውን ስነ ዘዴ ማዘጋጀት፣ የሰው ኃይል ማሰልጠን፣ ለመስክ ሥራ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ማሟላትና የቴክኖሎጂ ዝግጅትን ማካተት እንደሚያጠቃልል ከተቋሙ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

CapitalNews

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በመንገድ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ

አደጋው የደረሰው ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ...

ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች  565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት...

የአማርኛ ቋንቋ እውነተኛ ምንጭ ቤተ መንግሥት ሳይሆን ሕዝብና ሠራዊት ነው

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም አዘጋጅነት ከስድስት...