Date:

ባለስልጣኑ ‘በባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ የዝሆኖች ቁጥር አነስተኛ ሆኗል’ የሚለው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን በቆጠራ አረጋግጫለሁ አለ

በኢትዮጵያ ትልቁ የዝሆኖች መጠለያ በሆነው እና በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን በሚገኘው የባቢሌ ፓርክ፤ “የዝሆኖች ቁጥር አነስተኛ ሆኗል” በሚል የተሰራጨው መረጃ የተሳሳተ ስለመሆኑ በቆጠራ ማረጋገጡን የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

“የፓርኮች ዋነኛው ሥራ በውስጣቸው ያለውን የዱር እንስሳት ቁጥር ማወቅ ነው” ያሉት የባለሰልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኩመራ ዋቅጅራ፤ በዓመት በደረቅ ሁኔታ ቢያንስ ለሁለት ግዜ ቆጠራ እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡

ቆጠራው በወቅቶች ላይ ልዩነት እንደሚኖረው የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሩ፤ “ይህም በእንስሳት ብዛት እና ስርጭት ላይ ለውጥ የሚኖረው ጉዳይ ነው” ብለዋል፡፡

ሁሉንም ቆጠራ ማካሄድ ባይቻል እንኳን ዋና ዋናዎቹ ላይ ቆጠራ እንደሚካሄድ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣኑ ይገልጻል፡

“ዝሆን ከፍተኛ ፋይዳ ያለው እንስሳ ነው” የሚሉት አቶ ኩመራ፤ የሥነ-ምህዳር ማሀንዲስ የሚባል ስያሜ ሁሉ የተሰጠው በመሆኑ በፓርክ ውስጥ መኖሩ የሚሰጠው ጠቀሜታ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የአንዱ ዝሆን መኖር ለሌላው መኖር ጭምር መሆኑን የሚያነሱት ዳይሬክተሩ፤ “በዱር እንስሳት ውስጥ አንዱ ያለ አንዱ መኖር ከባድ ነው” ሲሉ አክለዋል፡፡

በመሆኑም ቁጥሩ ስለበዛ ስላነሰ ሳይሆን በአጠቃላይ ዝሆን ካለ ፋይዳው ከፍተኛ መሆኑ የተነሳ ሲሆን፤ ይህንን የተዘባ አስተሳሰብ ማረም ይገባል ብለዋል፡፡

ባለስልጣኑ በቅርቡ በባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ ላይ የዝሆን ቆጠራ ማካሄዱን የገለጹም ሲሆን፤ ቁጥሩን ግን ይፋ ማድረግ እንደማይፈልጉ ተናግረዋል፡፡

በዚህ መሠሰት ከሦስት ሳምንት በፊት የዝሆኖች ቆጠራ መካሄዱን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፤ “የቁጥሩ ማነስ በከፍተኛ ሁኔታ ሊያሳስበን ይችል ነበር ነገር ግን ይህ አልሆነም” ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በአጠቃላይ “በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያው የሚሰራጨውና ‘ለእርሻ መሬት ቢውል ይሻላል’ የሚል ሀሳብ ከግንዛቤ እጥረት የመጣ ነው” ሲሉም ገልጸዋል።

አሐዱ ራዲዮ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አርሰናል ከቦርንማውዝ በጉጉት የሚጠበቅ ጨዋታ

በ32ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ዛሬ ቀን...

በአሜሪካ እና ኢራን ድርድር ላይ የሚነሱ አራት ቁልፍ ጥያቄ

በፓኪስታን የሚደረገው የአሜሪካ እና የኢራን ድርድር እየተጠበበፓኪስታን ነገር ግን...

መንገዳችን ረጅም፣ ጉዟችን ፈታኝ መሆኑን እናውቃለን

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል...

የተመድ ዋና ጸሐፊ ኢራን እና አሜሪካ “በቅን ልቦና” ወደ ድርድሩ እንዲገቡ ጠየቁ

የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ አሜሪካ እና ኢራን...