ፎረሙ ከ ሰኔ 30 እስከ ሀምሌ 2 ቀን 2017 አ ም ድረስ በአዲስአበባ ይካሄዳል ተብሏል ፡፡
በግብርናው እና ኢኮኖሚ ዘርፍ ላይ የሚያተኩረዉ ፎረሙ በዓድዋ ድል መታሰቢያ እንደሚካሄድ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል አስታዉቀዋል ፡፡
በተጨማሪም በፎረሙ ላይ ከ1 ሺህ 500 በላይ ከተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ይሳተፋሉ ብለዋል ፡፡
ፎረሙ ላለፉት ሁለት ተከታታይ ዓመታት እንደ አህጉር ያለውን እምቅ ሃብት ወደ ተጨባጭ አቅም ለመቀየር ዕድል በሚፈጥር መልኩ መካሄዱን አስታውሰዋል።
3ኛዉን የአፍሪካ የስራ እድል ፈጠራ ፎረም ላይ ኢትዮጵያ ከብሄራዊ መታወቂያ ጋር ተያይዞ ያላትን ልምድ ለሌሎች የአፍሪካ አሃገራት ልምዶን እንደምታካፍል በመግለጫዉ ላይ ተነግሯል ፡፡
