3ኛው ኢንቨስት ኢትዮጵያ ከፍተኛ የቢዝነስ ፎረም በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው

Date:

የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት ዕድል ለማስተዋወቅ ያለመው 3ኛው ኢንቨስት ኢትዮጵያ ከፍተኛ የቢዝነስ ፎረም ከግንቦት 4 እስከ 5 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ይካሄዳል።

ይህ ፎረም በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን (ኢኢኮ)፣ በገንዘብ ሚኒስቴር እና በልማት አጋር ድርጅቶች ትብብር የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።

ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር) በሰጡት መግለጫ፣ ፎረሙ አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችን ለመሳብ፣ መንግስት ለዘርፉ ያለውን ከፍተኛ ትኩረት እና አዳዲስ የፖሊሲ ማሻሻያዎችን ለማስተዋወቅ እንደሚረዳ አመልክተዋል።

ባለፈው ዓመት በተካሄደው 2ኛው የኢንቨስት ኢትዮጵያ የቢዝነስ ፎረም ከ750 በላይ ድርጅቶች መሳተፋቸውንና ከ1.6 ቢሊዮን ዶላር በላይ ኢንቨስት ለማድረግ ቃል የተገባበት እንደነበር አስታውቀዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የምርጫ ካርድ፡ የአገር ባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ

ግዮን መጽሔት :- በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ጉዞ ውስጥ ምርጫዎች የሥልጣን...

አደይ ኢትዮጵያ ጓል አስመራ…!!

የቀድሞ ፕ/ት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የስንብት ቃል ለጠቅላይ ሚ/ር ዐብይ...

ትራምፕ ከኢራን ጋር በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ሁለተኛው ዙር ድርድር ሊደረግ እንደሚችል ተናገሩ

ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የሚደረገው ሁለተኛ ዙር የሰላም ድርድር...

በ”ፊንቴክ” ኢንቨስትመንት በተጠረጠሩት ላይ ተጨማሪ ጊዜ ተፈቀደለት

ፖሊስ ተጨማሪ 14 ቀን ለምርመራ እንዲፈቀድለት ባለፈው አርብ በነበረው...