4 ሺሕ 520 ወጣቶች በሚድሮክ እርሻ ሥራ ላይ እንዲሰማሩ ተደረጉ

Date:

በመዲናዋ በ2017 በጀት ዓመት 10 ወራት ውስጥ ውሎና አዳራቸውን ጎዳና ላይ ያደረጉ 4 ሺሕ 520 ወጣቶችን ከጎዳና ላይ በማንሳት፤ በሚድሮክ ኢትዮጵያ የቡና እርሻ ሥራ ላይ እንዲሰማሩ መደረጉን የአዲስ አበባ ሴቶች፣ ሕጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስታውቋል።

በቢሮው የማህበራዊ ሴፍቲኔት እና ኑሮ ማሻሻያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ቢኒያም ግርማ፤ ወጣቶቹ በሚድሮክ ኢትዮጵያ ሥር በሚተዳደረውና በጅማ ከተማ በሚገኘው በበቃ የቡና እርሻ ልማት ውስጥ በቡና ለቀማ እና ተመሳሳይ ዘርፎች ላይ የሥራ ዕድል እንደተፈጠረላቸው ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

አያይዘውም በተያዘው በጀት ዓመት በአጠቃላይ 27 ሺሕ 802 የሚሆኑ ጎዳና ላይ የሚኖሩ ዜጎችን በማንሳት፤ ወደ ማገገሚያ ማዕከላት በማስገባት የተለያዩ ድጋፎችና ስልጠናዎችን በመስጠት ወደ ማህበረሰቡ መቀላቀል መቻሉን ገልጸዋል።

ከእነዚህም ውስጥ 26 ሺሕ 221 ወንዶችና 1 ሺሕ 581 የሚሆኑት ደግሞ ሴቶች መሆናቸውን ገልጸው፤ ምግብና አልባሳትን ጨምሮ የተለያዩ የሥነ-ልቦና እና የሕክምና ድጋፎች ሲደረግላቸው መቆየቱን ተናግረዋል።

በዚህም መሠረት ወደ ማገገሚያ ማዕከሉ ገብተው ስልጠና እንዲወስዱ ከተደረጉት መካከል 4 ሺሕ 520 የሚሆኑ ወጣቶችን በዋነኝነት በአዲስ አበባ ያለው የሥራ አማራጭና ፍላጎት የማይመጣጠን በመሆኑ፤ ከሚድሮክ ኢትዮጵያ ጋር በመነጋገር ወደ ሥራ እንዲገቡ በትኩረት ሲሰራበት መቆየቱን ገልጸዋል።

ይህም ዜጎችን ከጎዳና ላይ የማንሳት ሥራ በፍላጎታቸው ላይ ተመስርቶ እንደሚሰራ የገለጹት ዳይሬክተሩ፤ “በሚድሮክ የቡና እርሻ ውስጥ የሥራ ዕድል ከተፈጠረላቸው በተጨማሪ፤ 3 ሺሕ 200 የሚደርሱ ሕጻናትን ወደተለያዩ ክልሎች በመመለስ ከወላጆቻቸው ጋር እንዲቀላቀሉ ተደርጓል” ብለዋል።

አክለውም ቤተሰባቸውን ማግኘት ያልተቻሉ 20 የሚሆኑ ሕጻናትን ደግሞ፤ ሴቶች፣ ሕጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሥር ባለው ተቋም ገብተው የትምህርት አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉን አንስተዋል።

ጎዳና ላይ ከሕጻን እስከ አረጋውያን እንዲሁም ሴቶችና ወንዶች ሁሉም አይነት ዜጋ እንደሚገኝ የገለጹት ዳይሬክተሩ፤ 100 የሚደርሱ አረጋውያንን ከመቄዶንያ እና ሰንሻይን የአረጋውያን መርጃ ማዕከል ጋር ትስስር በመፍጠር ዘላቂ የሆነ አገልግሎት እንዲያገኙ ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋል።
(አሐዱ ሬዲዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ንባብ ለሕይወት ባዛር እየተካሄደ ነው !!!

በንባብ ለሕይወት ፕሮጀክትና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አዘጋጅነት የሚካሄደው...

በኢራን የኤነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠረ አዲስ መጠነ ሰፊ ጥቃት መታቀዱ ተሰማ

የአሜሪካ ጦር በዚህ ሳምንት መጨረሻ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት...

የብሔር ፌደራሊዝምን ለማስቀጠል “የቆረጡ” ተመካካሪዎች

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 14ኛ ቀን ውሎ “ስልታዊ” ቡድኖች የአጀንዳ...

“የሩሲያ ክርስቲያኖች ከኢራን ሙስሊም ማህበረሰብ ጋር መልካም ግንኙነት አላቸው” ፓትርያርኩ

የሩሲያ ክርስቲያኖች ከኢራን ሙስሊም ማህበረሰብ ጋር መልካም ግንኙነት አላቸው...