49 ሰዎችን አሳፍሮ የነበረ የሩሲያ አዉሮፕላን ተከሰከሰ

Date:


43 መንገደኞችንና 6 ሠራተኞችን አሳፍሮ ይበር የነበረ አንድ የሩሲያ የመንገደኞች አዉሮፕላን ሩሲያን ከቻይና ጋር በሚያውስነዉ ድንበር አካባቢ ተከሰከሰ።

አንቶኖቭ 24 (A-24) የተባለዉ አዉሮፕላን  ዛሬ ጧት ሩሲያን ከቻይና ጋር ከሚያዋስነዉ ድንበር ላይ ከምትገኘዉ ብላጎቬሽሼንስክ ከተባለችዉ ከተማ ትይንዳ ወደተባለች ሌላ ከተማ መብረር ላይ ነበር።

አዉሮፕላኑ አሳፍሯቸዉ ከነበሩት ሰዎች በሕይወት የተረፈ መኖሩ ብዙ አጠራጥሯል።አዉሮፕላኑ በወደቀበት አካባቢ ቀድመዉ የደረሱ የአደጋ ሠራተኞች በእሳት የተቃጠለ የአዉሮፕላኑን ሥብርባሪ ማግኘታቸዉን አስታዉቀዋል።

አዉሮፕላኑ ይበር በነበረበት አካባቢ «አስቸጋሪ» የዓየር ሁኔታ ነበር ከመባሉ በስተቀር የአደጋዉ ትክክለኛ መንስኤ አልታወቀም።


(ፎቶ፣-የተከሰከሰዉ አዉሮፕላን ዓይነት፣ A-24)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ውጭ ምንዛሪ የሚያድኑ የሴራሚክ ምርቶች በቅርቡ ለገበያ ይቀርባሉ

ይህ የተገለፀው ኢትዮደር ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በ”Golden Tier...

የዓለም የቡና ገበያ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱ ተገለጠ

በዓለም አቀፍ ደረጃ በቡና አቅርቦት ላይ ተፈጥሮ የነበረው ስጋት...

አሜሪካ የኢራንን የጭነት መርከብን መያዟን አስታወቀች

በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ወደ ኢራን ወደቦች የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን የዘጋችው...