በአዲስ አበባ ከተማ ካሉ የደረጃ “ሀ” እና ደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮች ውስጥ 55ሺህ የሚሆኑት ነገዴዎች በቁርጥ ግብር ሲስተናገዱ እንደነበር ተገለፀ ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ካሉ የሂሳብ መዝገብ እንዲዙ ከሚገደዱ ከ1 መቶ 1 3 ሺህ በለይ የደረጃ “ሀ” እና ደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮች ውስጥ 55ሺህ የሚሆኑት ነጋዴዎች በቁርጥ ግብር ሲስተናገዱ እንደነበር የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ገልጷል ፡፡
ግብር ከፋዩ በህጉ መሰረት የሂሳብ መዝገብ ከመያዝ ይልቅ በተለያዩ ምክንያቶች በቁርጥ ግብር ለመስተናገድ ካለው ፍላጎት እንደሆነ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የህዝብ ግንኙነነት ዋና ዳይሪክተር አቶ ሰውነት አየለ ተናግረዋል፡፡
የሂሳብ መዝገብ እንዲይዙ በህግ የሚገደዱ ግብር ከፋዮች ከመጪው ሀምሌ 1 ቀን የግብር ማሳወቂያ ወር ጀምሮ ግን የተሟላ የሂሳብ መዝገብ በመያዝ ካልመጡ በስተቀር አይስተናገዱም ሲል አቶ ሰውነት አስታውቀዋል፡፡
የሚዘጋጀው የሂሳብ መዝገብ ደግሞ ሙያዊ አውቀት ባለው ባለሙያ መዘጋጀት አለበት ያሉት ዋና ዳይሪክተሩ ግብር ከፋዮች የሂሳብ መዝገብ ለማዘጋጀት የሚያስችል ዝግጂት ከወዲሁ ማድረግ እንደሚገባቸው ጠቁመዋል:
ኢትዮ ኤፍ ኤም
