724 ፕሮጀክቶች ግንባታ ላይ መሆናቸውን የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ

Date:

በኦሮሚያ ክልል 724 ፕሮጀክቶች ግንባታ ላይ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን ከዛ ዉስጥም 12ቱ ተጠናቀዉ ለምረቃ መዘጋጀታቸዉንና እስከ ሰኔ ተጠናቀዉ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆኑ የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ አስታዉቋል ።

38ቱ በተለያዩ የፀጥታ ችግር ግንባታቸዉ የተቋረጠ ሲሆን በአጠቃላይ በክልሉ የሚገኙ ሆስፒታሎች 120 መድረሳቸዉ ተገልጿል ። የመድኃኒት ፣የሰዉ ሀይል እና የህክምና ቁሳቁስ እጥረት ህዝቡ አሁን ላይ እያነሳ ያለዉ ጥያቄ በመሆኑ ይህን ለመቅረፍ 567 የህዝብ ፋርማሲዎች በከተማ ፣በወረዳ እና በሆስፒታል ደረጃ መስፋፋታቸውን የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶክተር ቦቆና ጉታ ተናግረዋል ።

ያጋጠመዉን የመድኃኒት አጥረት ሙሉ ለሙሉ ለመቅረፍ እንደ ክልል ብቻ ሳይሆን እንደ ሀገር ሰፊ ጊዜ በመዉሰድ መስራት እንደሚገባ የገለፁት ኃላፊዉ 80 በመቶ የሚሆነዉ መድኃኒት ከዉጪ የሚገባ በመሆኑ በሀገር ምርት መተካትና ለዚህ የሚዉለዉን በጀት መጨመር ትልቁ ለወደፊት የሚሰራ በዕቅድ የተያዘ ነዉ ብለዋል ።

ጤና ኬላዎችንና ጤና ጣቢያዎችን በማስፋፋት አዳዲስ አሰራሮችን በመዘርጋት በፊት ያልነበሩ 10 ሆስፒታሎች ዉስጥ የሲቲ ስካን አገልግሎት መጀመሩን ዶክተር ቦቆና ከጣቢያችን ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል።

@ብስራት ራዲዮ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ጥቃት አድራሹ ከካሊፎርኒያ መሆኑን ትራፕ ገለፁ

ትናንት ቅዳሜ ምሽት በዋይት ሃውስ የጋዜጠኞች ማኅበር የእራት ግብዣ...

በኬንያ የመንገደኞች አውሮፕላን ከመስመሩ ወጥቶ ተከሰከሰ

ዛሬ ረፋድ ላይ በኬንያ ማንዴራ የአውሮፕላን ማረፊያ አንድ...

አቶ ጀማል አህመድ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨማሪ 26 ሚሊየን ብር ሰጡ

አቶ ጀማል አህመድ ባሳለፍነው ወር ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ  ከሰጠው...

“የቻይና-አፍሪካ የምርምር ማዕከል”በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሊከፈት ነው

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከቻይና-አፍሪካ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር "የቻይና-አፍሪካ የምርምር...