በመዲናዋ ባለፉት አራት ወራት ከ5 ሺህ በላይ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎች ላይ የደረሰኝ ቁጥጥር በመካሄድ ከ954 ሚሊዮን ብር በላይ ደረሰኝ እንዲቆረጥ ማድረጉን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አስታውቋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት አራት ወራት በ5 ሺህ 203 የደረቅ ጭነት ተሸከርካሪዎች ላይ የደረሰኝ ቁጥጥር ማካሄዱን ገልፆል፡፡
የደረሰኝ ቁጥጥሩ በሁሉም የከተማዋ አቅጣጫዎች ወደ ከተማዋ በሚገቡ፣ከከተማዋ በሚወጡና በከተማዋ ውስጥ በሚንቀሳቀሱ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎች ፣ሚኒባሶችና አነስተኛ ሽፍን መኪኖች ላይ እየተካሄደ ነው፡፡
በዚህም ያለደረሰኝ ጭነት በመያዝ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 907 የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን 1 ሺህ 39 ግብር ከፋዮች ደረሰኝ እንዲቆርጡ 997 ግብር ከፋዮች ላይ ደግሞ አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዷል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ በተደረገው የቁጥጥር የደረቅ ጭነት ተሸከርካሪዎቹ የጫኗቸው ሸቀጦች ላይ የ954 ሚሊዮን 803 ሺህ ብር ደረሰኝ እንዲቆረጥባቸው ለማድረግም ተችሏል፡፡
በአሁኑ ወቅትም የደረሰኝ ቁጥጥሩ በቀን ብቻም ሳይሆን በለሊት ጭምር ተጠናክሮ መቀጠሉ የተገለፀ ሲሆን ደረሰኝ ሳይዙ ሸቀጥ በመጫን በሚንቀሳቀሱ ተሸከርካሪዎች ላይ ከሚወሰድ አስተዳደራዊ እርምጃ በተጨማሪ በቀጣይ የደረቅ ጭነት አሽከርካሪዎቻቸው ላይም የህግ ተጠያቂነት እንዲሰፍን የሚደረግ መሆኑ ቢሮዉ አስታውቋል።
