ትራምፕ የዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ ባንክ ኃላፊ በአስቸኳይ ስራ እንዲለቁ ጠየቁ

Date:

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በጄሮም ፓውል ላይ የሰነዘሩትን ትችት በማጠናከር የፌደራል ሪዘርቭ ሊቀመንበር በአስቸኳይ ስራ እንዲያቆሙ ጠይቀዋል።

ትራምፕ የግል ንብረታቸው በሆነው ትሩዝ  የማኅበራዊ መድረክ ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ “‘በጣም ዘግይቷል’ በአስቸኳይ ስራ መልቀቅ አለባቸው” ብለዋል።

በተጨማሪም ፓውል በማዕከላዊ ባንክ ዋሽንግተን ዋና መሥሪያ ቤት እድሳት ላይ በሰጡት ምስክርነት ላይ ምርመራ እንዲደረግ የዩናይትድ ስቴትስ ፌዴራል የቤቶች ተቆጣጣሪን ገልፀው ተናግረዋል።

ትራምፕ በመጀመሪያ የስልጣን ዘመናቸው ፓውልን የፌዴሬሽኑ ሊቀመንበር አድርገው ሾመዋል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የወለድ ምጣኔን አልቀነሰም በማለታቸው ደጋግሞ ሲወቅሰው ቆይተዋል።

ነገር ግን ፕሬዚዳንቱ ከስልጣን የማውረድ ስልጣናቸውን እስከምንድ ድረስ እንደሆነ ግልፅ አይደለም።

ፕሬዚዳንቱ በ​​ፓውል ላይ ትችታቸውን ቢቀጥሉም ፣ በዚህ አመት መጀመሪያ ላይ “ፓውልን የማባረር ምንም ፍላጎት እንደሌላቸው” ተናግረዋል ።

ትራምፕ የኢኮኖሚ እድገትን ለማሳደግ የፌደራል ሪዘርቭ የወለድ ተመኖችን እንዲቀንስ ይፈልጋሉ። ፓውል እንደተናገሩት የትራምፕ የታሪፍ ፖሊሲዎች ተጽዕኖ ባይኖራቸው ኖሮ ፌዴሬሽኑ ቀድሞውኑ ተመኖችን ይቀንስ ነበር ብለዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በኬንያ የመንገደኞች አውሮፕላን ከመስመሩ ወጥቶ ተከሰከሰ

ዛሬ ረፋድ ላይ በኬንያ ማንዴራ የአውሮፕላን ማረፊያ አንድ...

አቶ ጀማል አህመድ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨማሪ 26 ሚሊየን ብር ሰጡ

አቶ ጀማል አህመድ ባሳለፍነው ወር ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ  ከሰጠው...

“የቻይና-አፍሪካ የምርምር ማዕከል”በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሊከፈት ነው

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከቻይና-አፍሪካ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር "የቻይና-አፍሪካ የምርምር...

በኢትዮጵያ በማሳደጊያ ተቋማት የሚገኙ ሕፃናት ቁጥር ወደ 12 ሺሕ ዝቅ አለ

በኢትዮጵያ በተለያዩ የሕፃናት ማሳደጊያ ተቋማት ውስጥ የሚገኙ ሕፃናት...