የሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ የሚታየውን ችግር ለመፍታት ያለመው መርሃግብር

Date:

  በብሩህ ማይንድስ ኮንሰልት የተዘጋጀውና ለሶስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው ልዩ ምልከታ የኢንተርፕርነርሺፕ መርሃ ግብር መጠናቀቁ ተገለፀ።

ከ4000 ሰው በላይ ጎብኚዎችና 40 ተሳታፊዎች የታደሙበት ልዩ ምልከታ የኢንተርፕርነርሺፕ ውይይት መርሀግብርና የገንዘብ አቅርቦት ለሥራ ፈጣሪ ኢንተርፕራይዞች የተሰኘው አውደ ርዕይ በኢትዮጵያ የሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ የሚታየውን ችግር ለመፍታት ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

በ5ኛው ዓመታዊ የልዩ ምልከታ የኢንተርፕርነርሺፕ አውደርዕይ እና የፓናል ውይይት ላይ ለጀማሪ ሥራ ፈጣሪ ወጣቶች እና ለአነሥተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች መሠረታዊ ማነቆዎች በሆኑ የብድር አቅርቦት ፈተናዎች ዙሪያ መፍትሄ አመላካች የሆኑ የፖሊሲ ግብዓት ምክረ-ሀሳቦች ቀርበዋል፡፡

ከዚህ ጎን ለጎን በሰሞንኛው አውደ-ርዕይ እና መድረክ ላይ ጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች በቀላሉ ገንዘብ የሚያገኙበትን አማራጮች ለመፍጠር ከአበዳሪ ድርጅቶች የማገናኘት ስራ መከናወኑን የሁነቱ አዘጋጅ የብሩህ ማይንድስ ኮንስልት መስራች አቶ ሰለሞን ደሳለኝ ተናግረዋል።

ብሩህ ማይንድስ ኮንሰልት የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ላይ ጥናትና ምርምር፣ ሥልጠናዎችንና የንግድ ልማት አገልግሎት የሚያከናውን አማካሪ ተቋም ነው።

ተቋሙ የሥራ ፈጠራና ወጣቶች ልማት ለማሻሻል በሚደረጉ ጥረቶች ውስጥ የበኩሉን አዎንታዊ ሚና ለመጫወት ብዙ ጥረት እያደረገ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ከነዚህ ጥረቶች ውስጥ አንዱ የሥራ ዕድልና የሥራ ፈጠራን ለማበረታታት ባለ ድርሻ አካላት በቅርበት በመወያየት የተሻለ ከባቢ እንዲፈጠር “ልዩ ምልከታ” የተባለ መድረክ አዘጋጅቶ ላለፉት አምስት ዓመታት ሲያከናውን መቆየቱን ጠቅሷል።

(ሀገሬ ቴቪ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ካናዳ ምዝገባም ሆነ ስምሪት አልተጀመረም

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መቀመጫውን ካናዳ ካደረገው "ፊውቸር ፊት ኢንተርናሽናል"...

የክቡር ዶክተር ጋሽ መሐሙድ አዲስ አልበም ለአድማጮች ሊደርስ ነዉ

ታዋቂው ድምፃዊ ክቡር ዶክተር አርቲስት መሐሙድ አሕመድ «ለታሪክ» የተሰኘውንና...

ሜታ ‘ፌስቡክ እና ኢንስታግራም በቀረበባቸው ክስ 18 ቢሊዮን ዶላር ለመክፈል ተስማማ

ግዙፉ የማኅበራዊ ሚዲያ ኩባንያ ሜታ በፌስቡክ እና በኢንስታግራም ምክንያት...