የመድፈኞቹ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ አዲሱ ፈራሚያቸው ማርቲን ዙቢሜንዲ ” ትልቅ የእግርኳስ እውቀት አለው ” ብለዋል።
“ ዙቢሜንዲ ለቡድኑ ጥራት እና ትልቅ የእግር ኳስ እውቀት ይጨምራል “ ሲሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ተናግረዋል።
ማርቲን ዙቢሜንዲ ጨዋታ የመረዳት እና መተንተን አቅሙ ከፍ ያለ መሆኑን የገለፁት አርቴታ ያለው አቅም የቡድናቸውን አቅም ያሳድጋል ብለዋል።
” ተጨዋቹ ለቡድናችን በትክክል ይስማማል የቡድኑ ቁልፍ ተጨዋች የሚያደርገው ሁሉም ባህሪ አለው “ አርቴታ
