ኢራን ሰላም እንዲመጣ ከተፈለገ የዓለም አቀፉ የአቶሚክ ሀይል ድርጅት በትክክለኛ መርህ ላይ መቆም አለበት በሚል አስጠነቀቀች።
ድርጅቱ (IAEA) በአንድ አፍ ሁለት ምላስ “ደብል ስታንዳርድ” ዓይነት አካሄዱን መተው አለበት ባይ ናት ኢራን።
በቴህራን የኑክሌር መርሃ ግብር ዙሪያ ትብብር ከተፈለገ ራፋኤል ግሮሲ መራሹ አይ ኤ ኢ ኤ ፍትሃዊ አካሄድ ሊኖረው እንደሚገባ ተነግሯል፡፡
የኢራኑ ፕሬዚዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን ለአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አንቶኒዮ ኮስታ የኢራን ከድርጅቱ ጋር መተባበራችንን የምንቀጥለው አንዱን ለመጥቀም ሌላውን ለመጉዳት የሚደረጉ ጥረቶች ሲቆሙ ብቻ ነው ብለዋቸዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ በኢራን ላይ ጥቃት የሚሰነዘር ከሆነ አደገኛ ምላሽ እንሰጣለን በሚልም አረጋግጠዋል።
“ለጥቃቱ ምላሽችን ጠላቶቻችን የሚጸጸቱበት ይሆናልም “ባይ ናቸው ማሱድ ፔዜሽኪያን።
በቴህራን እና በአይ ኤ ኢ ኤ መካከል የነበረው ትብብር ከመቋረጡም ባሻገር በአሁኑ ሰዓት ፖለቲካዊ መካሰስ ውስጥም ናቸው።
በተለይም በ12 ቀናቱ ጦርነት የድርጅቱ ቁመና ወላዋይ ነበር የሚል ቅሬት ቴህራን በተደጋጋሚ እያቀረበች ይገኛል፡፡
ዋሽንግተን ፖስት ዘግቦታል፡፡
