አዲስ አበባ እና የህንጻ እድሳት

Date:

በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ሰፍራዎች ከ24 ሺህ በላይ አዳዲስ ህንፃዎች በግንባታ ላይ ናቸው ተባለ። ይህን ያለን የከተማዋ የግንባታ ፈቃድ ባለስልጣን ነው ።

ግንባታዎቹ ለተለያዩ ማህበራዊ  ኢኮኖሚያዊ ለንግድ ማዕከላት የሚውሉ ሲሆኑ ለከተማ አጠቃላይ ዕድገት፣ ኢኮኖሚያዊ መነቃቃትና የሥራ ዕድል ፈጠራ ትልቅ ጥቅም እንዳላቸው  ተቋሙ ገልጾልናል ።

ይህ በእንዲህ እንዳለም በአዲስ አበባ የህንፃዎች ግንባታ የደህንነት አጠባበቅ ከፍተኛ ክፍተት ያለበት እንደሆነ መገምገሙን ሰምተናል።

ይህን መልክ ለማስያዝ  የግንባታ የደህንነት መመሪያዎች በተገቢው መልኩ እንዲተገበሩ አሳስቧል ።

ቀደም ብሎም በጥቅሉ በከተማዋ የሚገኙ የህንፃ ባለቤቶች ከ11 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ 24 ሺህ ህንፃዎችን ደረጃቸውን ጠብቀው እንዲታደሱ ተደረገዋል ።

በዚህም የከተማዋን ድረጃ ከፍ ከማድረጋቸውም ባሻገር ለበርካቶች የስራ እድልን መፍጠራቸወን  ተገልጿል ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...