የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽነሮች መልቀቂያ ማስገባታቸውን ተገለፀ

Date:

የኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መለሰ እና የሴቶች፣ ሕፃናት፣ አካል ጉዳተኞች እና አረጋዊያን መብቶች ኮሚሽነር የሆኑት ርግበ ገ/ሐዋርያ ባለፈው ሳምንት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸውን ምንጮችች ገልፀዋል።

ኮሚሽነሮቹ ለምክር ቤቱ የሦስት ወር ማስጠንቀቂያ ጊዜ መስጠታቸውን ምንጮች የተናገሩ ሲሆን፤ ስለ ሥራ መልቀቂያው ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ለተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች በዋና ኮሚሽነሩ በኩል እንደተነገረ ቢቢሲ ከምንጮቹ ተረድቷል።

የከፍተኛ ኮሚሽነሮቹ የሥራ መልቀቅ ከአዲሱ ዋና ኮሚሽነር “የአመራር ስልት” ጋር በተያያዘ “ተገፍተው” ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የኮሚሽኑ ምንጮች ለቢቢሲ ተናግረዋል።

“አሳታፊነትን” ይከተል የተነበረው የተቋሙ አሠራር ባለፉት ወራት ለሥራ ኃላፊዎች እና ለሠራተኞቹ ውሳኔዎቹን “አለማሳወቅ፣ አለማሳተፍ እና መመካከርን” ወደ ጎን ማለቱ ለኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራሮች መልቀቅ እንደ አንድ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል አመልክተዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በመንገድ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ

አደጋው የደረሰው ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ...

ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች  565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት...

የአማርኛ ቋንቋ እውነተኛ ምንጭ ቤተ መንግሥት ሳይሆን ሕዝብና ሠራዊት ነው

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም አዘጋጅነት ከስድስት...