በኒውዮርክ በተደረገ የጂኦሎጂካል እና አርኪኦሎጂካል ጨረታ በምድር ላይ ትልቁ እና የሚታወቀው የማርስ ቁራጭ በ5.3 ሚሊዮን ዶላር ተሽጧል።
ኤን ደብሊው ኤ 16788 የተሰየመው የማርስ ሜትሮይት 25 ኪሎ ግራም ይመዝናል። በኒጀር ሳሃራ በረሃ በኖቬምበር 2023 ከማርስ በኃይለኛ የአስትሮይድ ፍንዳታ ከተመታ እና 225 ሚሊዮን ኪሎ ሜትር ወደ ምድር ከተጓዘ በኋላ ተገኝቷል።
ሜትሮይት በምድር ከባቢ አየር ውስጥ እና በመሬት ላይ በመጓዝ የሚገኝ የኮሜት ፣ የአስትሮይድ ወይም የሜትሮይድ ቁርጥራጮች ናቸው።
ለሜቲዮራይት የመጨረሻው ጨረታ 4.3 ሚሊዮን ዶላር ቢሆንም፣ አጠቃላይ ዋጋው 5.3 ሚሊዮን ዶላር ደርሷል። የገዢው ማንነት እስካሁን አልተገለጸም ሲል ሶስቴቢስ የተሰኘው የጨረታውን ያዘጋጀው ተቋም ገልጿል።
በጨረታ ቤቱ “የማይታመን ብርቅዬ” ቀይ-ቡናማ አለት ተብሎ የተገለፀው ሜትሮይት በምድር ላይ ከተገኙት 400 የሚጠጉ የማርስ ሚቴዮራይቶች አንዱ ነው።
በተጨማሪም በምድር ላይ ከሚገኙት ሁለተኛው ትልቁ የማርስ ክፍልፋይ በ70 በመቶ የሚበልጥ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ በፕላኔታችን ላይ ከሚገኙት የማርስ ቁሳቁሶች 7 በመቶ ያህሉን ይወክላል።
