ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ከዲላ ዩኒቨርሲቲ እና ከዲላ ከተማ አስተዳደር ጋር ተፈራረመ

Date:

መግባቢያ ሰነዱ የጎዳና ተዳዳሪ ሕጻናትን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል ነው ተብሏል።

የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ በበኩላቸው፣ የስምምነት ሰነዱ በከተማው የሚገኙ የጎዳና ተዳዳሪዎችን ኑሮ ለማሻሻል እና ታዳጊ ሕጻናቱን ከጎዳና ለማንሳት የሚያስችል መሆኑን ገልፀው፣ የዲላ ከተማ አስተዳደርም ለስራው የሚያስፈልግ ቦታዎችን ዝግጁ በማድረጉ አመስግነዋል።

የዲላ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ሀብታሙ ተመስገን (ዶ/ር)  በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ እንደገለጹት፣ ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተፈራረመው የመግባቢያ ሰነድ፣ በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ የመጣሁን የጎዳና ተዳዳሪ ሕጻናትን ቁጥር ለመቀነስ፣ ዘርፉ ላይ አረጋውያንና ሕጻናትን በዘላቂነት በማቋቋም በርካታ ልምድ ካለው ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት እንደሆነ ገልጸዋል።

በከተማው በጎዳና ተዳዳሪ ሕፃናት ላይ እየታየ ያለውን ችግር በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመፍታት 1ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ዝግጁ ተደርጓል ያሉት የዲላ ከተማ አስተዳደር ተወካይ አቶ ቸርነት ማርያም ፤ አስተዳደሩ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ሜሪጆይኢትዮጵያ #ኢትዮጵያዊያን_ለኢትዮጵያዊያን

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

“ቴዲ አፍሮ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ቀይሮታል!” — ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

በ"ወቸው ጉድ" ፖድካስት ላይ እንግዳ ሆነው የቀረቡት ፕሮፌሰር ብርሃኑ...

የኢራን ጦር የሆርሙዝ ወሽመጥን በድጋሚ መዝጋቱን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ

የኢራን መገናኛ ብዙኃን የአገሪቱ ጦር የሆርሙዝ ወሽመጥን ዳግም መቆጣጠር...

ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ስኩል 20ኛ ዓመት ክብረ በዓል

ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ስኩል 20ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን አስመልክቶ...

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለ20 አትሌቶች  የማስጠንቀቂያ አውጥቷል

በውድድሩ ላይ ያልተገኛችሁ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይመለከታል የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዓለምአቀፍ...