በኢትዮጲያ ግዙፍ የአውሮፕላን ጥገና ማዕከል ተመረቀ

Date:

የኢትዮጲያ አየር መንገድ እጅግ ዘመናዊ የአውሮፕላን ጥገና ወርክሾፕን ጨምሮ ፥ ዘመናዊ መጋዘንን አስመርቋል።

አየር መንገዱ ይህንን ዘመናዊ ልዩ ልዩ የአውሮፕላን ጥገና ማዕከላት የተካተቱበትን ግዙፍ ማእከል ከ 150 ሚሊየን ዶላር  በላይ በማውጣት  ማስገንባቱን የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው በምረቃው ወቅት ተናግረዋል።

በ150 ሚሊየን ዶላር ወጪ የተደረገባቸው  ፕሮጀክቶች የአውሮፕላን ክፍሎች መጠገኛ፣ የአውሮፕላን ጥገና ማዕከል እና ከሰው ንከኪ ነፃ የሆነ መጋዘን  ናቸው።

የጥገና ቁሳቁሶች የሚከማቹበት መጋዘኑ  በ15 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ መሆኑ ተገልፃል።

የኢትዮጵያ አየር ሀይል ዋና አዛዥ እና የአየር መንገዱ የቦርድ ሰብሳቢ ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ፣ እና ሌሎች  የተቋሙ እና የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ፣ዲፕሎማቶች እንዲሁም በፕሮጀክቱ የተሳተፍ አካላት በምረቃው ወቅት ተገኝተዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...

ትራምፕ ኢራን ላይ ያላቸው ትዕግሥት እየተሟጠጠ መሆኑን ተናገሩ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው መሪ ዢ ጂንፒንግ ጋር...