ከክልሎች የሚፈልሱ ታዳጊ ህፃናትን መልሶ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለማቆየት ፈታኝ ሆነ

Date:

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች፣ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ከክልሎች ወደ አዲስ አበባ የሚፈልሱ ታዳጊ ህፃናትን ወደ ቤተሰቦቻቸው የመቀላቀል ስራ ቢሰራም በሚፈለገው መልኩ ውጤታማ አለመሆኑን ገለጸ።

ያም ሆኖ በተጠናቀቀው በጀት አመት 17 ሺህ የሚሆኑ ህፃናትን ወደ ትውልድአካባቢያቸው መመመለሱን ጠቅሶ፥ አብዛኛዎቹ ወደ ኦሮሚያ፣ ሲዳማና ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መመለሳቸውን ነው ቢሮ የተናገረው።

ቢሮው በክልሎች ላይ ህፃናቱ ከቤተሰቦቻቸው ጋር በቋሚነት ለመኖር የሚያስችላላቸውን ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ረገድ በጋራ እየተሰራ ባለመሆኑ ችግሩ ሊቀረፍ አለመቻሉን ገልጿል።

በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ለተለያዩ ማህበራዊ ቀውስ፣ ለጉልበት ብዝበዛ፣ሱስና ፆታዊ ጥቃት ጭምር የተጋለጡ ህፃናቶች መኖራቸውም ተመላክቷል።

የአራዳን ገጾች በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኮሪያ ዘማቾች ያስመዘገቡት አኩሪ ታሪክ በዓለም ሲታወስ ይኖራል

75ኛ ዓመት የኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ በዓል አዲስ አበባ በሚገኘው...

አሜሪካ በጣለችው የባህር ላይ እገዳ ሳቢያ ኢራን 4.8 ቢሊዮን ዶላር አጣች

በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትዕዛዝ በኦማን ባህረ ሰላጤ ላይ...

ኢሕአፓ ሊያካሂድ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ማራዘሙን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ሚያዚያ 30 ቀን 2018...

እሁድ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ ይደረጋሉ

መነሻውንና መድረሻውን መስቀል አደባባይ የሚያደረገው ዓለም አቀፉ የዛይድ የበጎ...