እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የልባችሁን መልካም መሻት ትሙላላችሁ !!!

Date:

በአንቺ አማላጅነት፣ በልጅሽ ምሕረት የታምንሁ ነኝ

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነቷና ተራዳኢነቷ በብዙ መልኩ ዛሬም ድረስ ያልተለየን የዘለዓለም ቃል ኪዳን የተገባላትና በቃል ኪዳኗም አማልዳ የምታስምር ናት፡፡

በመዝሙር 88÷3 “ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳን አደረግሁ” ተብሎ እንደተጻፈው ለመረጣቸው ቃል ኪዳን የሰጣቸው አምላካችን እግዚአብሔር ማደሪያው ትሆን ዘንድ ለመረጣት ለእናቱ ለቅድስት ድንግል ማርያም ከሌሎች ቅዱሳን በተለየ ይህን ቃል ኪዳን አብዝቶ ሰጥቷታል፡፡ ”መታሰቢያዋን የሚያደርግ፣ ስሟን የሚጠራ፣ ለድሆችና ለችግረኞች እስከ ቀዝቃዛ ውኃ የሚሰጥ” የአማላጅነት የእናትነት ቃል ኪዳን በነፍስም በስጋም ይጠብቀዋል፡፡

ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት “በወርቅ ልብስ ተጎናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች” ሲል በመዝሙር 44÷9 እንደገለጸው ከፍጥረት ሁሉ በላይ ነችና በቀኙ ቆማ በተሰጣት ቃልኪዳን ታማልደናለች፡፡   

የዐሥራት ልጆቿ እኛ ክርስቲያኖችም ዘወትር “ንጽሕት ድንግል ማርያም የታመነች አምላክን የወለደች ናት። ለሰዎች ልጆችም የምሕረት አማላጅ ናት እንላለን። የቅዱስ ኤፍሬምን አንደበት አንደበታችን አድርገንም ኃጥአታችንን ያስተሠርይልን ዘንድ ወደ ልጅሽ ወደ ክርስቶስ ለምኝልን” እያልን እናመሰግናታለን እንለምናታለን።

ከአባታችን አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ጋርም በእሑድ አርጋኖን “ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ! እታመንሻለው፤ ከተሠወረው መከራ፣ በግልጽ ከሚመጣብኝ ጥፋት ሁሉ በዚህ ዓለም እንድታድኚኝ።

በሚመጣውም ዓለም ከገሃነመ እሳት ጥርስ ማፋጨት ጽኑ ለቅሶም ካለበት፣ ከሚያስጨንቅ መቅሠፍትም ትሠውሪኝ ዘንድ፣ እኔም በአንቺ አማላጅነት፣ በልጅሽ ምሕረት የታምንሁ ነኝ።

በፈረሰኞች ሰልፍ በሠረገላም መንኮራኩር የምታመን አይደለሁም በአንቺና በልጅሽ እታመናለው እንጂ።” እያልን እንማጸናታለን፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስ የእመቤታችን አማላጅነት በማያሻማ ሁኔታ የታየበት የዮሐንስ 2÷3 ነው፡፡ ፍቁረ እግዚእ፣ ቁጽረ ገጽ እየተባለ የሚገለጸ ወንጌላዊው ዮሐንስ በዶኪማስ ሠርግ ቤት ጌታችን ከእናቱና ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ተገኝቶ ነበር በማለት በሚያነሳው ታሪክ “የወይን ጠጃቸውም ባለቀ ጊዜ እመቤታችን ልጇ ወዳጃን “የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም” በማለት ነግራዋለች፡፡

ወይኑ እንዳለቀባቸው ማንም ሳነይነግራት የፊትን መጥቆር የልብን ኀዘን የምትረዳ ከዓይን ጥቅሻ ፈጥና የምትደርስ እናታችን እመቤታችን፣ ወሳኝ በሆነ ሰዓት ለቃና ሙሽሮችም ፈጥና ነበር የደረሰችላቸው፣ ከውርደትም ያዳነቻቸው። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የሰው ችግር ቶሎ የሚገባት፣ ቶሎ የሚታያትና የሚሰማት ርኅርኅት እናት መሆኗን አባቶች ይናገራሉ።

በቃና ገሊላም ችግራቸውን ፈጥና የተረዳች እመቤታችን ልጇን ፍጹም ትሑት በሆነ መንገድ ጠየቀችው እንጂ ልጄ ነው ብላም አላዘዘችውም፤ “ባለ ውለታህ ነኝ” ብላም ማሳሰቢያ አልሰጠችም፤ ብቻ “ወይን እኮ የላቸውም” ብላ እጅግ በሚጣፍጥ ትሕትና ለመነችው፡፡

ልጇ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ልመናዋን ሰምቶ ውኃን ወደ ወይን ለውጦላቸው የመጀመሪያውን የአምላክነት ምልክት በሠርጉ ቤት አድርጓል፤ በዚህም የእመቤታችን ምልጃ በጎላ በተረዳ ነገር ታውቋል። እመቤታችን ለሰው ልጆች ያላት ፍቅርና ርኅራኄ በሰውና በመላእክት አንደበት ተነገሮ የሚያልቅ አይደለም፡፡

ገዳማውያን አባቶችም ይህን ምልጃዋን ተስፋ በማድረግ በሌሊትና በቀን ሰዓሊ ለነ ቅድስት ይሏታል፡፡ ገዳማቸውን ስነደግፍ በዓታቸውን ስናጸና በእኛም ላይ በረከቷ ያድርብናል፡፡
 
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ 1000442598391
ወይም አቢሲኒያ ባንክ 141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ኔታንያሁ እና ትራምፕ የፊታችን ማክሰኞ በዋይት ሀውስ እንደሚወያዩ ተገለጸ

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት፤ ቤንያሚን ኔታንያሁ ከፕሬዝዳንት ዶናልድ...

አሜሪካ በኢትዮጵያ ያላትን የንግድና ኢንቨስትመንት ትብብር ለማጠናከር ከኢትዮጵያ መንግሥትና ከግሉ ዘርፍ ጋር ውይይት አካሄደች

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ጄ. ማሲንጋ፣ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን...

የካፍ ፕሬዝዳንት የ2027 አፍሪካ ዋንጫ በ24 ተሳታፊ ሀገራት እንደሚካሄድ አስታወቁ

የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን (ካፍ) ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሙትሰፔ የ2027...

የቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ነፃ የጤና ምርመራና ሕክምና መስጠት ጀመረ

ሆስፒታሉ በቀን ከ300 በላይ ታካሚዎችን ያስተናግዳል የቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ከሐምሌ...