የፈረንሳዩ ተቋም መልቲቾይዝ ግሩፕን በ3 ቢሊየን ዶላር ገዛ

Date:

ካናል+ መጀመሪያውንም ቢሆን የመልቲቾይዝ 45 በመቶ ባለድርሻ የነበረ ሲሆን አሁን ሙሉ ለሙሉ ድርሻውን ገዝቶታል።

መልቲቾይዝ ለ40 አመታት የቆየ ስም የገነባ መሆኑ ሲገለፅ በአፍሪካ ከ50 ሚሊየን በላይ ደንበኞች እንዳሉት ይገለፃል።

መልቲቾይዝ በክፍያ ከሚሰሩ የቴሌቪዥን ገበያዎች ውስጥ አንዱ ሲሆን በዲ ኤስ ቲቪ እና ጎቲቪ በኩል የተለያዩ የስፖርት እና የመዝናኛ ፕሮግራሞችን በክፍያ ሲያስተላልፍ ቆይቷል።

ግዢው ሙሉ ለሙሉ በመጪው ጥቅምት ይጠናቀቃል ተብሎ ሲጠበቅ ካናል+ የደቡብ አፍሪካን ፕሮዳክሽን በአዲስ ገበያዎች የማስተዋወቅ ኃላፊነት ተጥሎበታል።

ደቡብ አፍሪካ በህጓ የደቡብ አፍሪካን የስርጭት መብት የያዘ ድርጅት ባለቤትነቱ ከ20 በመቶ በላይ በውጪ ዜጋ መያዝን ስለምትከለክል መልቲቾይዝ የስርጭት መብቱን ላይሰንስኮ በተሰኘ ድርጅት ማድረጉ ተሰምቷል።

መልቲቾይዝ ሃገራችን ኢትዮጵያን ጨምሮ ብዙ ተጠቃሚዎች ያሉት ሲሆን በዲ ኤስ ቲቪ በኩል የእግር ኳስ እና የመዝናኛ ፕሮግራሞችንም ሲያሰራጭ ቆይቷል።

ካናል+ በበኩሉ ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ከገባ በኋላ የክፍያ ቴሌቪዥኑን በመዝጋት ወደ ሌላ አማራጮች ማዞሩን ከወራት በፊት መግለፁ ይታወሳል።

Source: tikvahethmagazine

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኮሪያ ዘማቾች ያስመዘገቡት አኩሪ ታሪክ በዓለም ሲታወስ ይኖራል

75ኛ ዓመት የኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ በዓል አዲስ አበባ በሚገኘው...

አሜሪካ በጣለችው የባህር ላይ እገዳ ሳቢያ ኢራን 4.8 ቢሊዮን ዶላር አጣች

በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትዕዛዝ በኦማን ባህረ ሰላጤ ላይ...

ኢሕአፓ ሊያካሂድ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ማራዘሙን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ሚያዚያ 30 ቀን 2018...

እሁድ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ ይደረጋሉ

መነሻውንና መድረሻውን መስቀል አደባባይ የሚያደረገው ዓለም አቀፉ የዛይድ የበጎ...